የቅዱስ ያሬድ አስተምሮ በሚገባ ታውቆና ተመርምሮ ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም መጥቀም እንዲያስችል ሥራ ለመስራት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡

የቅዱስ ያሬድ አስተምሮ በሚገባ ታውቆና ተመርምሮ ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም መጥቀም እንዲያስችል ሥራ ለመስራት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከኢትዮጵያ ያሬዳዊ ፍልስፍና፣ ጥበብ፣ ሥነ-ውበትና ክዋኔ ጥበብ ማበልጸጊያ ድርጅት ጋር በመተባበር የቅዱስ ያሬድ አስተምሮ በሚገባ ታውቆና ተመርምሮ ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም መጥቀም የሚገባውን ያህል ለመጥቀም የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመሥራት በቅድሚያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫና አውደ ምክክር መድረክ አስመልክቶ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚካሔደው ሀገራዊ ጉባሔ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫውን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው ተቋሙ የባህል ተቋሙ እንደመሆኑ መጠን ሀገር በቀል እውቀቶችን የሚሰበስብና የሚያደራጅ በመሆኑ የቅዱስ ያሬድ አስተምርኦ ምን ሊጠቅም እንደሚችል የምክክር መድረክ እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡

የተቋሙ የአብያተ መጻሕፍትና የሰነድ ስልጠናና ማማከር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ መኮንን ከፍያለ የምክክር መድረኩ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲናገሩ የቅዱስ ያሬድ ወርቃማ አስተምሮ ላይ ጉባኤ ለማካሄድ እንደሆነና የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የተለያዩ ጉባኤዎችን ከዚህ ቀደም እንደሚያዘጋጅና በሚሰራቸው ሥራች ላይ ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረውና የቅዱስ ያሬድ ወርቃማ አስተምሮ ለሀገሪቱ ካለው አበርክቶ አንጻር የምንፈትሽበትንና የምናይበትን ተከታታይ ጉባኤ ለማዘጋጀት እንደሚረዳም ጠቁመዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ያሬዳዊ ፍልስፍና፣ ጥበብ፣ ሥነ-ውበትና ክዋኔ ጥበብ ማበልጸጊያ ድርጅት የመጡት ልጅ ወንድሜነህ ለዓከማርያም እንዳሉት የቅዱስ ያሬድ ወርቃማ አስተምሮቶች እስካሁን ያልደበዘዙት በወርቅ ቢጻፉ ነው፤ ስለዚህ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው የሚለውን ከመንፈሳዊ አባቶች እና በተለያየ ዘርፍ ያሉ ልሂቃኖች ጋር በመሆን ከሀገራዊ እስከ አለም አቀፋዊ ጉባኤ ለማድረግ የታለመ እንደሆነም ተናግረው

አክለውም ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን ለማወቅ የውጭ ጸሃፍትን ሳይሆን ቅዱስ ያሬድን የመሰሉትን ማወቅ ግድ ይለናል ያሉት ልጅ ወንድሜ ነህ ከተቋሙ ጋር መስራታችን ስኬታማ እንሆናለን በሚል ነው ብለው የግዕዝ ጉባኤ ዘላቂነትና ስኬታማነትን ላይ ተንተርሰው ተናግረዋል፡፡

በስተመጨረሻም ሁለቱም ተወካዮች ይሔ የካቲት 21 የሚካሔደው የመጀመሪያው ዙር ጉባሔ ለወደፊት በስፋት ለማካሔድ መደላድል እንደሆነና በአውደ ውይይቱ ላይ ምሁራን፣ አባቶች፣ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ሚዲያዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ቀጥተኛ ተጋባዥ እንደሆኑም ተናግረው ከጋዜጠኞች ለተጠየቁ ጥያቄዎች በጋራ ምላሽ ሰጥተው ጋዜጣዊ መግለጫው ተጠናቋል፡፡

Share this Post