የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የመማክርት ጉባኤ አቋቋመ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የመማክርት ጉባኤ አቋቋመ::
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ሰነድና መዛግብትን ለማስተዳደርና ለማስወገድ በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን የመማክርት ጉባኤ አቋቋሙ።
የመማክርት ጉባኤው አዋጅ 179/91 በደነገገውና ለይቶ ካስቀመጣቸው ተቋማት የተወከሉ አባላት የተውጣጡበት ሲሆን ማክሰኞ መስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም የትውውቅና የመጀመሪያ የስራ ሂደት ምክክርን አድርጓል።
በዚህ መርሐ ግብር የመማክርት ጉባኤው ስብሳቢ የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ተወካይ አቶ ወርቅነህ አክሊሉ እና የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ይህን የመማክርት ጉባኤ የማቋቋም አስፈላጊነትና በቀጣይ የሚጠበቁ ስራዎችን ለአባላቱ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በተቋሙ የሰነድና መዛግብት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ጠና የመማክርት ጉባኤና ሰነድ ማስወገድን የተመለከተ ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።