በዱራሜ ከተማ የመጽሐፍ ስጦታ እና የንባብ ክበባት ምስረታ መርሐግብር ተከናወነ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከደቡብ ህዝቦች ብሔር ብሔረሰቦች ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ከየካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በዱራሜ ከተማ ባዘጋጀውየንባብ ክበባት ምስረታ እና አውደ ውይይት መርሐግብር ላይ አራት አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን ከተማሪዎቻቸው ጋር እንዲሁም የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት  ተቋሙ ለ8 ት/ቤቶች እና ለህዝብ ቤተመጽሐፍቱ 2600 መጽሐፍት በገንዘብ ሲተመን 489,961.90 ወጪ በማድረግ በስጦታ የማበርከትና የንባብ ክበባት ምስረታ መድረክን በዱራሜ ከተማ የህዝብ ቤተ መጽሐፍት ተከናውኗል። 
በዚህ መርሐግብር ደራሲ ዘነበ ወላ፣ ሀያሲ ገዛኸኝ ሀብቴ፣ ደራሲ ሊዲያ ተስፋዬ፣ ደራሲና መምህር ሰለሞን ዮሐንስ፣ ደራሲና መምህር አለሙ ባንቱ እና ሌሎችም የንባብ ልምድና ተሞክሮአቸውን ያቀረቡ ሲሆን ተማሪዎች ማብራሪያ እና ጥያቄዎችን በማቅረብ የንባብ ልምዳቸውን ለማዳበር የሚያስችል የተሞክሮ ምክክር አድርገዋል።

Share this Post