"የጥምቀት በዓል ባህላዊ እሴቶቻችንን ፤አብሮነታችንን ፤ አንድነታችን ለዓለም የምናሳይበት በዓል ነው" የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር

"የጥምቀት በዓል ባህላዊ እሴቶቻችንን ፤አብሮነታችንን ፤ አንድነታችን ለዓለም የምናሳይበት በዓል ነው" የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር  ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ  የጥምቀትን በዓል አስመልከቶ በሰጡት መግለጫ  ወቅት እንደተናገሩት በዓሉ  ከሀይማኖታዊ ክብረ በዓል በሻገርነት ባህላዊ እሴቶቻችንን ፤አብሮነታችንን ፤ አንድነታችን ለዓለም የምናሳይበት ነው ብለዋል። 
  ቱሪስቶች ይህንን በአል አስመልከቶ ከተለያዩ የአለም ሀገራት ወደ ሀገራችን የሚመጡበትና ሀገራችንም በርካታ የውጪ ምንዛሬ ምታገኝበት  ክብረ በዓል ነው ሲሉ ገልጸዋል  ፡፡  
 የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዲኤታ ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ በበኩላቸው በዓሉ ባህላዊ እሴቶቹ ተጠብቆ እንዲሁም ይዘቱን ሳይለቅ ከትውልድ ወደ ትውልድ ከማሻገር እና ከማስተዋወቅ አኳያ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ስራ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የማህበረሰብ አካል ሀላፊነት እንደሆነ አስታውቀዋል ፡፡   
የሚዲያ አካላት ከበዓሉ ጋር ተያይዞ የሚከናወኑ ባህላዊ እሴቶቻችንን   ለተቀረው የአለም ክፍል የማስተዋወቅ ትልቅ ስራ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡   
በዓላቱ በሚከበርባቸው ስፍራዎች ወጣቱ  በዓሉ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ  እና የሀገራችንን ገጽታ በሚያሳይ መልኩ እንዲከበር ከእምነት አባቶችን እና ከጸጥታ ሀይሎች ጎን በመሆን የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል ፡፡

Share this Post