በጂንካ ከተማ የንባብ ሳምንት፣ አውደርዕይ እና ተንቀሳቃሽ የሕፃናት ቤተ-መጻሕፍት በይፍ ተከፈተ።

ጷጉሜ 2/ 2017 ዓ.ም

"የንባብ ባህል ለት/ት ጥራት!" በሚል መሪ ቃል በጂንካ ከተማ አንድነት ፓርክ የተሰናዳው የንባብ ሳምንት፣አውደርዕይ እና ተንቀሳቃሽ የሕፃናት ቤተ-መጻሕፍት በይፍ ተከፈተ።

አቶ የሰዉዘር በላይነህ በትምህርት ሚኒስቴር የሚኒስትር  ዴኤታ አማካሪና  የሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ፣ አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ፣ አቶ ሲሳይ ጋልሺ የጂንካ ከተማ ከንቲባ ፣ ወ/ሮ ጸሐይ ወራሳ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ት/ት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ውብሸት ደግነት  የወርልድ ቪዥን ደቡብ ፕሮግራም ጽ/ቤት ኃላፊ እንደዚሁም ጥሪ የተደረገላቸው ታዳምያን ተንቀሳቃሽ የሕፃናት ቤተ- መጻሕፍቱንና አውደርዕዩን ጎብኝተዋል።

በመቀጠል  አለም አቀፍ የንባብ ቀንን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት ተደርጓል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት በትምህርት ሚኒስቴር የሚኒስትር  ዴኤታ አማካሪና  የሚኒስቴር ዴኤታ ተወካይ  አቶ የሰዉ ዘር በላይ የት/ት ፍኖት ካርታ ጥናት በሚጠናበት ወቅት መሠረታዊ የት/ት ጥራት ችግር የንባብ ክህሎት ችግር መሆኑ በግልፅ እንደተለየና ሁሉም ዜጋ በአፍ መፍቻ ቋንቋው እንዲማሩና እንዲያነቡ ማድረግ የመፍትሄ ምክር ሐሳብ  ተብለው ከተቀመጡ ነጥቦች መካከል አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

በመርሐ ግብሩ መልዕክታቸውን ያጋሩት የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት የንባብ ክህሎትና የንባብ ባህል በሁለት አበይት ጉዳዮች፡- 

ከመሰረታዊ ክህሎት አንዱ አካል በመሆኑና የእድሜ ልክ የማይቋጭ የየዕለት ተግባር በመሆኑ የሁላችን ዋና ጉዳይ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት  ንባብ በአንድ አዳራሽ ተወስኖ የሚቀር ነገር ባለመሆኑ በመላ የሀገሪቱ ክልሎች በመዘዋወር የንባብ ባህልን በማስፍፍት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የፓናል ውይይቱን መነሻ የንባብ ባህልን ስለማዳበር የሚያትት ጥናታዊ ፅሑፍ ዶ/ር ብርሀኑ ቦጋለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ  የንባብ ጥምረት የቴክኒክ ቡድን መሪና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ  አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

በጂንካ ከተማ የተዘጋጀውን የንባብ  ሳምንት፣ አውደርዕይ፣ ተንቀሳቃሽ የሕፃናት  ቤተ-መጻሕፍት እና የፓናል ውይይቱን የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ት/ት ቢሮ እና ወርልድ ቪዥን " የንበብ ባህል ለትምህርት ጥራት! " በሚል መሪ ቃል በመተባበር አዘጋጅተውታል።

Share this Post