የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የስም ስያሜ ተቀየረ

ጥቅምት 5/2019 ዓ.ም
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት 1ኛ ልዩ ስብሰባው የፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ስያሜ፣አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በአዋጅ ቁጥር 1440/2019 አድርጎ በሙሉ ድምፅ ሲያጸድቅ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ስያሜ ወደ «የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት ባለስልጣን» መቀየሩን ይፋ አድርጓል ።
በዚሁ መሠረት የቀድሞው «የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ስያሜ ወደ «የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት ባለስልጣን» የተቀየረ ሲሆን በዚህም መሠረት ላይ ብቻ ተወስኖ የሚገኘው የተቋሙ አሠራር መዋቅሩን ታች ድረስ ለመዘርጋት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርለታል።

Share this Post