19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ
ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት
"ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!"በሚል መሪ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት፤የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ፣ፋና ሚድያ ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር በጋራ በድምቀት አክብረዋል።
በዓሉን በማስመልከት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ሥራ አመራር አቶ አብነት አበራ ዛሬ የሚከበረው ብሔራዊ በዓል ኢትዮጵያውያን የሀገርን ዳር ድንበር እና ክብሯን ለማስጠበቅ ደምና ላባቸውን አፍስሰው፣አጥንታቸውን ከስክሰው ያስከበሩት ሠንደቅ ዓላማ በጋራ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሠንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር የመስጠትና የማክበር ኃላፊነትና ግዴታ እንዳለበት በአጽንኦት ተናግረዋል።
በዓሉን በማስመልከት ንግግር ያደረጉት የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቸሩጌታ ገነነ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ትናንት አባቶቻችን በከፈሉት መስዋትዕነት ያልተደፈረች ሀገር መውረሳችንን ገልጸው
አክለውም የሠንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ትናንት መስዋዕትነት የከፈሉትንና ዛሬም ለኢትዮጵያ አንድነት የሚዋደቁትን የሰላምና የጸጥታ አካላትን በማክበር ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በዝግጅቱም በፌደራል ፖሊስ በዓሉን በማስመልከት ትርኢት ቀርቦ ሠንደቅ ዓላማው ተሰቅሎ ተጠናቋል።