ሰማንያ( 80) የንባብ አመታት፡፡

ሰማንያ( 80) የንባብ አመታት፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በመጪው ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም  የሚያከብረውን 80ኛ አመት የምስረታ በአል እና አዲስ ያስገነባውን የቤተመዛግብት እና የቤተመጽሃፍት አገልግሎት ህንጻ ምረቃ አስመልክቶ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የመዛግብት ህንጻ ምርቃት እና ተቋሙ የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ እንደተናገሩት ተቋሙ ጥልቅ የሀገር የእውቀት ሀብት መያዙን ጠቁመው በአሁኑ ወቅት የህንጻ ማስፋፊያ ስራ መከናወኑ በውስጡ ያለ የእውቀት ሃብት ተጠብቆ እንዲቀጥል እና በተሻለ ደረጃ ተደራሽነት ለመጨመር እንደሚረዳ ገልጸዋል ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት አጠቃላይ ህንጻው ሰባት መቶ ሚሊየን ብር የፈጀ ሲሆን በአንድ ሺህ አራት መቶ /1400 /ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ባለ 17 ወለል ሲሆን የመዛግብት ህንፃው የስነ- ጥበብ ሊቁ  ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ በተቋሙ ውስጥ ለነበራቸው መስሪያ ቦታ መታሰቢያ ሊሆን የሚችል የስዕል ኤግዚቢሽን ስፍራን ጨምሮ በዋናነት ለመዛግብት ማከማቻ የሚያገለግል እንዲሁም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘና በተለይም ስለ ንባብ እና መዛግብት ለሚደረጉ ሁነቶች በሰፊው የሚውል አምስት መቶ /500/ ሰው መያዝ የሚችል አዳራሽ አለው፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች መልሶች ተሰጡ ሲሆን የምረቃ ስነስርአቱ እና ተቋሙ 80ኛ አመት ምስረታ በአል የካቲት 16 ቀን 2016 ክቡራን ሚኒስተሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሐይማኖት መሪዎች እንዲሁም አንባቢዎች በተገኙበት በይፋ እንደሚያስመርቅ ተገልጿል። በተጨማሪም ከምረቃው እለት አንስቶ የተቋሙን ስራ የሚየሳዩ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በትብብር የተዘጋጁ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን፣ የድምጽ ኤግዚቢሽን፣ የጥንታዊ  ጽሁፎች ( የእስልምና እና የክርስትና) ኤግዚቢሽኖች እና የመጸሃፍት እና የአሳታሚዎች ኤግዚቢሽን ለህዝብ ጉብኝት ይፋ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

Share this Post