የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከተለያዩ ተቋማት የተሰበሰቡ 718 ሊኒየር ሜትር ወይም ከ5,744 ቦክስ ፋይል በላይ ሰነዶችን ወደ አገልግሎቱ በማዛወር ቴክኒካል ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከተለያዩ ተቋማት የተሰበሰቡ 718 ሊኒየር ሜትር  ወይም ከ5,744 ቦክስ ፋይል በላይ ሰነዶችን ወደ አገልግሎቱ በማዛወር ቴክኒካል ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ አዋጅ ቁጥር 179/91  የመማክርት ጉባኤ ብሔራዊ የሰነድ ውገዳ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወቃል፡፡

የተቋቋመውን አዋጅ ተከትለው ከጥቅምት 2016 ዓ.ም ጀምሮ ምዘና እና መረጣ ሥራ ተደርጎላቸው የተመረጡ መዛግብትን ወደ ኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ያዛወሩ የፌደራል ዋና ኦዲተር እና በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሙገር ሴሚንቶ ፋብርካ ሲሆኑ ሰነዶችን ለማስወገድ ከአመንጪ ተቋማቱ ጋር ብሔራዊ የሰነድ ውገዳ ኮሚቴ በቅርብ ሲሠራ እንደቆየ የአገልግሎቱ የአብያተ መጻሕፍትና የሰነድ ስልጠናና ማማከር መሪ ሥራ አስፈጻሚ እና የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ መኮንን ከፋለ ተናግረዋል፡፡

ከሁለቱም ተቋማት 718 ሊኒየር ሜትር ወይም ከ5,744 ቦክስ ፋይል በላይ ወደ ኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በማዛወር ቴክኒካል ተግባራት ሲያከናወን እንደቆየና በአሁን ሰዓት ደግሞ በሰነዶቹ ላይ አስፈላጊውን የመጨረሻ ምርመራ ወይም ምዘና እየተደረገ  እንደሚገኝ ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡፡

አያይዘውም ዳግም ምዘና እስከ ግንቦት መጀመሪያ ሳምንት ዘላቂ ፋይዳ ያላቸውን መዛግብትን በመለየት ወደ መዛግብት ክምችት ክፍሉ በማዛወር ለውገዳ የሚለዩትን ሰነዶች ደግሞ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ሥራውን በማጠናቀቅ ለማስወገድ  እየተሠራ  እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

Share this Post