የኢፌዲሪ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ክብረት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ክቡር ሙላቱ ተሾመ ባለቤት ክብርት መአዛ አብርሃምታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት(ወመዘክር)በመገኘት ጎበገኙ፡፡

የኢፌዲሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ክብረት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤"በእውነቱ በዛሬው ዕለት በዚህ ከልጅነቴ ጀምሮ በማውቀው ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መጥቼ ይህንን ተአምራዊ ስራ ለማየት በመቻሌ በጣም ነው ደስ ያለኝ!"በማለት ገለጹ።

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን

ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም

የኢፌዲሪ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ክብረት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ክቡር ሙላቱ ተሾመ ባለቤት ክብርት መአዛ አብርሃም ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት(ወመዘክር)በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝታቸውም ተቋሙ  የሚሰጠው አገልግሎትን በሚመለከት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰርፀ ፍሬስብሐት እና የየክፍሉ ስራ አስፈጻሚዎች ገለጻ አድርገውላቸዋል።

ከጉብኝቱም በኋላ ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ"ድሮ እማርበት ከነበረው ሊሴ ገ/ማርያም ት/ቤት ወደ ለገሀር ስንሄድ ማለፊያው ነውና ጎራ እንላለን።

በጥልቀት ስለ ተግባሩ ባላውቅም ራስን ለማሳደግና ለማነጽ የሚያግዝ እና ወጣቶች እንዲመጡበት የሚጋብዝ ነበር። በዚህ ደረጃ አድጎ በማየቴ ደስ ብሎኛል"በማለት ተቋሙን በሚመለከት ያላቸውን ትዝታ አካፍለዋል።

ክብርት ሳህለወርቅ፤"ሀገራችን ታሪኳ ብዙ ውጣውረድ ያለው ነው። እዚህ ባለው ስብስብ ለኢትዮጵያ ያለ ሀሳብ፣ ምክር፣ለኢትዮጵያ ያለ ቁጭት ተቀምጧል። ጃንሆይም ይህንን ተቋም ሲመሰርቱ ታሪኳን አቆይታ ለትውልድ የማታስተላልፈው ለምንድነው? በሚል መነሻ ነው። ስለዚህም ይህንን ሰው ማየት አለበት።"በሚል የተቋሙን ሀገራዊ ፋይዳ ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የኢፌዲሪ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ክብረት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ክቡር ሙላቱ ተሾመ ባለቤት ክብርት መአዛ አብርሃም ተቋሙ ለትውልድ እና ለሀገር የታሪክ ባለቤትነትን እና የጥናት እና ምርምር ማዕከልነትን ለማስቀጠል ዜጎች የመረጃ ሀብቶች የሆኑትን የጽሑፍ ሰነዶች፣መዛግብትና የታተሙ እና ያልታተሙ ስራዎችን እንዲሁም ቀረጸ ምስልና ድምጽ ለኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) እንዲያበረክቱ፤ በዚህም የዜግነት ግዴታቸውን በመወጣት ታሪክን እንዲያስቀጥሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Share this Post