የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ እና ውይይት ተካሄደ።
የተከናወኑ ተግባራት የተቋሙን ግብ ማሳካታቸውን የሚፈትሽና በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት አፈጻጸማቸው ዝቅ ያሉ ተግባራትን በአዲሱ የበጀት አመት በተሻለ መልኩ ለመፈጸም አስፈጻሚና ፈጻሚው ከባለፈው በተሻለ መልኩ ሊሰሩ እንደሚገባ ሲመላከት፦
የተቋሙ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ክፍሎች እያንዳንዳቸው ያከናወኗቸውን ተግባራት እና ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች በጥልቀት ለውይይት አቅርበዋል።
በቀረበው የ2018 በጀት ዓመት ክንውን ሃሳብ አስተያየቶች እንዲሁም ጥያቄዎች ተነስተው የተቋሙ የጽ/ቤት ኃላፊ እና የዋና ዳይሬክተሩ ተወካይ አቶ አባተ ካሳው ምላሽ ሰጥተው ከሰራተኛው የተነሱ ሃሳብ አስተያየቶች አሁን ለተጀመርነው ለአዲሱ የበጀት ዓመት ግብዓት እንደሚሆኑና ወደተግባር ተቀይሮ ከተሰራበት ውጤቱ የላቀ እንደሚሆን ገልጸዋል።
በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ክንውን
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣አደጋና ስጋት ኮሚሽን፣ ብሔራዊ ባንክ በሠነድና መዛግብት አስተዳደር ሞዴል ተደርገው ለአብነት ከተወሰዱት መካከል ናቸው።
በቤተ መጻሕፍት ዘርፍ ደግሞ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ኮሪያ ሆስፒታል፣አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተጠቃሽ ነበሩ።
ስልጠና የወሰዱ ሰልጣኞች በተለይ የሪከርድ ምዘና እና መረጣ ሳይደረግ ሪከርዶች እንዳይወገዱ ተጨባጭ ስራዎችን መስራት፥
የቤተመጻሕፍት፣ የሠነድና የመዛግብት አስተዳደር ሙያዎቸ ላይ በሀገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚሰጡ ስልጠናዎቸ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ለሀገር ባላቸው ፋይዳ ማሳያ ማሳያ እንደሆኑ
2018 በጀት ዓመት በርካታ መዛግብት መሰብሰብና መደራጀት የተቻለበት ዓመት እንደነበር፤
ተቋሙን በርካታ ጎብኚዎች የመጎብኘት እና ሕትመቶችን በተመለከተ ጥሩ ክንውን የታየበት ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት የጎጃም መዛግብትን የያዘ ጥናታዊ መጽሔት መታተሙ
በግዥና በአዋጅ በርካታ የመረጃ ሀብቶች በተጨማሪ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት የትውስታ ተቋም (Memory institution) መሆኑን በጉልህ የሚያሳይ የፊት አውራሪ አመዴ ለማ ፣ የፕ/ር ተወልደ ገ/እግዚአብሔር እና የበርካታ ግጥምና ዜማዎች ፕሮዲውሰር ያየህይራድ አላምረው የግል ስብስቦች በሥጦታ ወደተቋም በማምጣት የተደራጁበት፤ የአቡነ ገሪማ ወንጌልን እና የሐረር የባቡር ዝርጋታ ዶክመንትን በአለም የጽሑፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ የተሰራው ጠንካራ ሥራ ተጠቃሽነት፤
ተዘጋጅተው የጸደቁ መመሪያዎች የአገልግሎት ክፍያ፤ የተሽከርካሪ ስምሪት አጠቃቀም የውስጥ መመሪያ፤የምድረ ጊቢ እና የህንጻ አስተዳደር የውስጥ መመሪያ የጸደቀበት ዓመት እንደነበር በቀረበው የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ክንውን ተመላክቷል።
ተግባራትን ከማከናወን አንጻር ጊዜያዊ መፍትሔዎች እየተሰጠ በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ስራዎች እንደተከናወኑ ተጠቁሞ በክንውናቸውም ዝቅተኛ አፈጻጸም አለመኖሩ በቀረበው 2018 ዕቅድ ክንውን ላይ ተመላክቷል።
የደጋፊ የሥራ ክፍሎች ክንውን በተቋሙ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ በአቶ አብነት አበራ ሲቀርብ፤የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ደግሞ በተቋሙ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አሥፈጻሚ በአቶ አህመድ ለውይይት ቀርቧል።
ዕቅድ ውይይቱ ሲጠናቀቅ በ2018 በጀት ዓመት የተቋሙን ዋና ተልዕኮ ዘመናዊ የሪከርድ ሥራ አመራር መዘርጋት መዛግብትን ማሰባሰብ፣የህትመት ውጤቶችን እና የጽሑፍ ቅርሶችን ማሰባሰብ፣ማደራጀት፣አገልግሎት እየሰጠ ለትውልድ ማስተላለፍ ሲሆን ይህንን እውን ለማድረግ እና እና ለዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ተቋማት ከወዲሁ ዝግጁ እንዲሆኑ ፊዚካል ሠነዶች የሚደራጁበት፣ የሚመረጡበት እና የሚወገዱበት አብያተመጻሕፍት ወቅቱን የዋጁ በሚሆኑበት ሁኔታዎች ላይ ሲሰራ እንደነበር ተጠቁሟል።
በመጨረሻም የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ውል ስምምነት እና ለግንባር ቀደም ፈጻሚዎች የምስክር ወረቀት እና የመጽሐፍ ስጦታ ተበርክቶላቸው ዝግጅቱ ተጠናቋል።