የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት 17ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል አከበረ
ኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት 17ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል አከበረ
ኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም በሚል መሪ ቃል ለ17ተኛ ጊዜ እንደ ሀገር የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ አክብሯል።
በዚህ መርሐግብር ላይ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች የዳቦ መቁረስ ፕሮግራም ሲከናወን በአቶ አህመድ መሀመድ የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ ህብረብሔራዊነት ላይ ያተኮረ እና ዓለም አቀፋዊ እውነታና ተሞክሮን ያካተተ የመወያያ ሰነድ እንዲሁም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስነ ምግባር መከታተያ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ክንፈ ሙስና እና ብልሹ አሰራርንና መገለጫዎቻቸውን ብሎም እንዴት መከላከል ይቻላል የሚለው ላይ የመወያያ ሰነድ አቅርበው በአቶ ሰለሞን አልዩ የሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጽ/ቤት ኃላፊ አወያይነት በተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።