ፍኖተ ንባብ በሚል መሪ ቃል ከሕዳር 16-18/2015 ዓ.ም ሲካሔድ የነበረው የንባብ ክበብ ምስረታና የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ተጠናቀቀ

ፍኖተ ንባብ በሚል መሪ ቃል ከሕዳር 16-18/2015 ዓ.ም ሲካሔድ የነበረው የንባብ ክበብ ምስረታና የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ተጠናቀቀ።
አንባቢ ሕጻናትና ወጣቶች የኢትዮጵያ ቤዛዎች ናቸው በሚል መልዕክት ለመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የንባብ ክበብ መመስረት ዓላማውና የወደፊት አካሔድ ላይ በአንጋፋው ደራሲ ኃይለ መለኮት መዋዕል ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሲሰጥ በደራሲ ለገሰ ኩሳ ወላጆችና ንባብ በሚል ሐሳብ የራሳቸውን የህይወት ተሞክሮ ለታዳሚው አካፍለዋል::
በዕለቱም ታዳጊ ቅዱስ የሸዋስ እና ህሊና የሸዋስ ንባብን በተመለከተ ለተማሪዎችና ወላጆች እንዲሁም ታዳሚዎች የግላቸውን የህይወት ተሞክሮ ሲያካፍሉ ሁለቱም መጻሕፍቶቻቸውን ለታዳሚዎች ሲያስተዋውቁ በቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር እና መልዕክት አዘል ሥነ ጽሑፎች ለታዳሚው ሲቀርቡ በመጨረሻም በጥያቄና መልስ ውድድር ለተሳተፉ ታዳጊዎች የምስጋና ምስክር ወረቀት በማበርከት ዝግጅቱ ተጠናቋል።

Share this Post