የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል እያከበረ ነው

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አንድነት፣ጀግንነትና ጽናት በሚል መሪ ቃል ለ127ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ ድል በዓል ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ከመከላከያ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በመኮንኖች ክበብ በተከፈተው ታሪካዊ አውደርእይ ላይ በመሳተፍ እያከበረ ይገኛል።

ይህ ልዩ መርሐግብር በመከላከያ ማርሽ ዜማ ተጀምሮ የባህል እና ስፖርት  ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ክቡር አቶ ቀጄላ መርዳሳ የአድዋ ድልን እንዲሁም አውደርእዩን አስመልክቶ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ዘንድሮ የአድዋን በዓል ታሪኩን በሚመጥን መልኩ ለማክበር ጥረት መደረጉን ገልጸዋል።

የአድዋ ድል በዓልን መሠረት ተደርጎ የተዘጋጀው አውደርእይን የባህል እና ስፖርት  ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ክቡር አቶ ቀጄላ መርዳሳ እና የመከላከያ ሰራዊት ጄነራሎች እና ከፍተኛ መኮንኖች በጋራ ከፍተውታል።

አውደርእዩ ቅድመ አድዋንና የአድዋ ድልን እንዲሁም ከሁነቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ስብስቦች ያካተተ ሲሆን ለሁሉም ህብረተሰብ ክፍል እስከ የካቲት 25 ቀን2015 ዓ.ም ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተገልጿል።

Share this Post