"አቡጊዳ" የተሰኘው የልጆች ንባብ ፌስቲቫል በድምቀት ተከፈተ

"አቡጊዳ" የተሰኘው የልጆች ንባብ ፌስቲቫል በድምቀት ተከፈተ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት
ከኪዲ ሰባት አስራሁለት ፊልም ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር ከጥር 5-7 ቀን2015 ዓ.ም "ልጆች ይችላሉ" "Children Can" በሚል መርህ በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል ያዘጋጀው የልጆች የንባብ ፌስቲቫል ጥር 5 ቀን 2015ዓ.ም በድምቀት ተከፍቶ ለታዳሚያን ክፍት ሆኗል።
መርሐግብሩን የከፈቱት እና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ተቋሙ የታዳጊ ካንሰር ህሙማንን እና የታዳጊ አይነስውራንን ቤተመጽሐፍት ለማሳደግ ይቻል ዘንድ በስጦታ ያዘጋጃቸውን  785 መጻሕፍት በብር ሲተመን ዋጋው 115,115.35 ብር የሆነውን አበርክተዋል።
በዚህ የመክፈቻ መርሐግብር በተቋሙ የሚገኙ እና በዩኔስኮ የተመዘገቡና ሌሌችም  የጽሑፍ ቅርሶች እንዲሁም የተቋሙ የአገልግሎት ፖርታል ገጽና የኤሌክትሮኒክ ንባብ ገጽ መረጃን የተመለከተ ዓውደርዕይ ብሎም በልጆች በቀረቡ የተለያዩ ዝግጅቶች የደመቀ ነበር።

Share this Post