የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ።
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከኪዲ ሰባት አስራሁለት ፊልም ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር ከጥር 5-7 ቀን2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል ለሚያደርገው የልጆች የንባብ ፌስቲቫልን አስመልክቶ በተቋሙ ቅጥሮ ግቢ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የተቋሙ የአብያተ መጽሐፍት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ተፈራ፣ ከኪዲ ሰባት አስራሁለት ፊልም ፕሮዳክሽን የዋና ስራአስኪያጅ ወ/ሮ ቅድስት ጆቴ እና ም/ስራአስኪያጁ አቶ ተመስገን ታደለ የ"አቡጊዳ" የተሰኘው የልጆች ንባብ ፌስቲቫል "ልጆች ይችላሉ" "Children Can" በሚል መርህ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚዘጋጅ እና በቀጣይ ዓመታዊ መርሐግብር ሆኖ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ተቋሙ ንባብ ላይ በመላው ሀገሪቱ ንባብ ላይ እንደሚሰራ የገለጹት አቶ ያሬድ፤ የንባብ መሠረት ልጆች በ መሆናቸው  በቀጣይም ለመረሐግብሩ  ቀጣይነት በትኩረት እንደሚሰራ አሳውቀዋል።
ይህ የልጆች የንባብ ፌስቲቫል እውን እንዲሆን
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከፍ ያለውን ሚና መጫወቱን በመጥቀስ ያመሰገኑት ወ/ሮ ቅድስት እና አቶ ተመስገን የመግቢያ ትኬቱ ከ12 ዓመት በታች ላሉ ህፃናት በነፃ እንዲሁም ለአዋቂዎች 100 ብር ሲሆን ከ15ሺህ እስከ 20 ሺህ ሰው ይካፈላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸው ማህበረሰቡ በዚህ የልጆች ንባብና የምክክር መድረክ፣ እየተማሩ የሚዝናኑበት ትዕይንቶች በተካተቱበት የንባብ ፌስቲቫል ላይ ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፈዋል።

Share this Post