የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ለተቋሙ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ለተቋሙ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ።
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከተቋሙ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች የጊዜ አጠቃቀም እና አመራር ላይ የባህሪ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም በተቋሙ አዳራሽ ሰጥቷል።
ስልጠናውን የሰጡት የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የለውጥ እና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብነት አበራ የጊዜ አጠቃቀም እና የስራ ውጤታማነት ያላቸውን ተያያዥነት በነባራዊ ሁኔታ ላይ መሰረት በማድረግ ያብራሩ ሲሆን መርሐ ግብሩ የተቋሙ ሰራተኞች ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ላይ የትኩረት ዕይታቸውን ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል።

Share this Post