መዛግብትን በአግባቡ ጠብቆ ለትውልድ ማሻገር እንደሚገባ ተገለጸ

መዛግብትን በአግባቡ ጠብቆ ለትውልድ ማሻገር እንደሚገባ ተገለጸ ፤ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣ ቤንች ሸኮ ዞን እና ሚዛን አማን ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ በጋራ "መጻሕፍት ለእውቀት ገበታ፤ መዛግብትና የጽሑፍ ቅርሶች ለዘመን ትውስታ" በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የንባብ ሳምንት ፣ ቡክፌር፣ የመጻሕፍት አውደ ርዕይና ኤግዚቢሽን  ከታሕሣሥ 15-18/2015 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ ከመርሐ ግብሩ መካከል የፖናል ውይይት በተቋሙ የዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በአብይ ርዕስ "መዛግብት የትናንት ፣የዛሬና የነገ አገናኝ ድልድይ" በሚል ርዕሰ የተዘጋጀ የመነሻ ጽሑፍ ለውይይት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በውይይቱም የሚመለከታቸው የበላይ አመራሬች፣ከተለያዩ ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የሪከርድ ባለሙያዎች ተገኝተውበታል።በአውደ ውይይቱ ላይም የመነሻ ጽሑፎች ከአገልግሎቱ በአቶ ግርማ አበበ የመዛግብት ጽንሰ ሐሳብና ጠቀሜታው፤በአቶ ሰለሞን ጠና መዛግብትን ከማሰባሰብና ከማደራጀት አንጻር ከማን ምን እንደሚጠበቅ፤በአቶ ስለሺ ሽፈራው የጥንታዊ ጽሑፎች መዛግብት ጥበቃና እንክብካቤ እና በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህር በእጩ ዶክተር አማረ ፈንታሁ የቤንች ሸኮ ዞን መዛግብት ስብስብ ላይ የመነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ከተሳታፊዎች አሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ተነስተው ጽሑፍ አቅራቢዎች ምላሽ ሲሰጡ የማጠናከሪያ አሳብና ምላሽ በአውደ ውይይቱ አወያይ በአቶ መኮንን ከፋለ ጥልቅ ምላሽ ተሰጥቶ ውይይት ተጠናቋል።

 

Share this Post