የትምህርት ቤቶች የንባብ ክበባት ምስረታና የንባብ ባህል የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረክ ተካሔደ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት፤ ሚዛን አማን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ ፤ ቤንች ሸኮ ባ/ቱ/ስፓርት መምሪያ እንዲሁም ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከታሕሣሥ 15-18/2015 ዓ.ም በጋራ ባዘጋጁት የንባብ ሳምንት፣ቡክፌር፣የመጻሕፍት አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት መድረክ እና ኤግዚቢሽን አካል የሆነው የትምህርት ቤቶች የንባብ ክበባት ምስረታና የንባብ ባህል የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረክ በቤንች ሸኮ ዞን ሁለገብ አዳራሽ እና አዳራሹ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ተካሒዷል።

የንባብ ክበብ ምስረታው ትኩረቱን ያደረገው የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የንባብ ክበብ ምስረታ ላይ ግንዛቤ የማስጨበጥ ነው። በመርሐ ግብሩ ታላላቅ ሰዎችና ደራሲያን የህይወት ልምዳቸውን እና የንባብ ክበባት በትምህርት ቤቶች መመስረት ስለሚኖረው ፋይዳ ያላቸውን ልምድ አካፍለዋል።

ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በመ/ር ዋለልኝ ደባልቄ የንባብ ምንነትና  ጠቀሜታው ላይ ፤በት/ት ቤቶች የንባብ ክበብ መመስረት ስለሚኖረው አስፈላጊነት ላይ በመምህር መሰረት አበጀ የግንዛቤ የማስጨበጥ የምክር አገልግሎት ለተማሪዎችና ለተሳታፊዎች ሲቀርብ በአንደኛ ደረጃ የትምህርት ቤቶች ላይም የንባብ ክበባት የመመስረትና የንባብ ባህል ላይ ግንዛቤ ከሚዛን ቴፒ ዩኒብቨርሲቲ መ/ር ሊድያ ተካ ንባብ እንዴት ሱስ ሊሆን እንደሚችል የንባብ ልምዷንና ተሞክሮዋን ስታካፍል በደራሲ ሊድያ ተስፋዬ በትምህርት ቤቶች የንባብ ክበባት መቋቋም ስለሚኖረው ጥቅም ቡድን በመመስረት ጥቅሙንበመቀጠልም ስታሳይ አቶ ፋሲል መንግስቱ ንባብ ህይወት ዓላማ ላይ ሰፊ ገለጻ በማድረ ግንዛቤ አስጨብጠዋል።

ከምክክር መድረኩ በመቀጠልም የተሳተፉት የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ መምህራን የራሳቸውን ተሞክሮና በአሁን ወቅት ንባብ ላይ ተማሪው ያለው ፍላጎት በጣም ውስን እንደሆነ በቅርበት የሚመለከቱትን በምሳሌ እያስደገፉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ተማሪዎች ንባብ ላይ ያላቸውን ተሞክሮ እንዲናገሩ የሚችሉት ምን ዓይነት መጽሐፍ ማንበብ እንዳለባቸው በቅርበት የሚነግር አንባቢ የሆነና ተምሳሌት ሊያደርጉት የሚችሉት የቅርብ ሰው እንደሌላቸው እንዲሁም ለማንበብ እንኳን ፍላጎቱ ቢኖራቸው በአካባቢያቸውና በትምህርት ቤታቸው ያሉት ቤተ መጻሕፍት ቤቶች ለማንበብ በሚፈልጉበት ወቅት ክፍት ሆነው አገልግሎት እንደማይሰጡ እና በጋጀብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስካሁን ድረስ ያልተማሩት የትምህርት ዓይነት እንዳለም ተናግረው እንዲህ አይነቱን ችግር ለመቅረፍና የተማሪውን የመጽሐፍት አቅርቦት ችግር ተረድቶ እንደ ሌሎች እድሉን እንዳገኙት የህዝብና የትምህርት ቤቶች ቤተ መጻሕፍት ቤቶች እድሉን የሰጠውን የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት አመስግነው እንደ ኢትዩጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስትም ትምህርት ዘርፉ ላይ ጠንክሮ በመስራት አንባቢ ትውልድ እንዲፈጠር የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም ተማሪዎቹ ጠቁመዋል።

Share this Post