የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር እና የመጻሕፍት ሰጦታ መርሃግብር ተካሄደ
የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር ተካሔደ
በቀን 16/2015 ዓ.ም በከሰዓቱ በኃላ መርሐ ግብር ላይ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የባህል ኪነት ቡድን እና የሚዛን አማን ከተማ የዞኑ የባህል ኪነት ቡድን መልዕክት አዘል ጭውውትና ግጥሞች በማቅረብ ተሳታፊውን አዝናንተዋል።
በእለቱን ወጣቱን ወደ ንባብ እንዲመጣ ሊያደርጉ የሚችሉ ተሞክሮዎች በመምህር መሰረት አበጀ፣በደራሲ ሊድያ ተስፋዬ እና በደራሲ ገዛኸኝ ሀብቴ በመቅረብ ተሳታፊዎች እንዲማሩበት ተደርጓል።
በመጨረሻም በሥነ ጽሑፍ መልዕክት ላካፈሉና ለተሳተፉ ተማሪዎች ማበረታቻ የተለያየ ዘውግ ያላቸው መጽሐፍት ተበርክቶላቸው የከሰዓቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል።
በተጨማሪ ዜና ሰማኒያ ዘጠኝ ሺህ ሦሥት መቶ ሰማኒያ አራት ብር የፈጁ መጻሕፍት ተበረከቱ
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት፤ ሚዛን አማን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣የደቡብ ምዕራብ ኢስፓርት ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ ፤ ቤንች ሸኮ ባ/ቱ/ስፓርት መምሪያ እንዲሁም ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር በጋራ ያዘጋጁት እና ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቆየው የንባብ ሳምንት፣ቡክፌር፣የመጽሐፍት አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት መድረክና ኤግዚቢሽን በሁለተኛ ቀን የጠዋቱ መርሐ ግብር ከሁለት ሺህ በላይ ታራሚዎች በሚገኙበት በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ማረሚያ ቤት የንባብ ቀን አካሒዳዋል።
በማረሚያ ቤቱ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ፣ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር አብዮት አስረስ ፣የደቡብ ምዕራብ ኢት/ያ ባህል ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ ተወካይ አቶ ወንድሙ ለማ፣ከቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ማረሚያ ቤት ም/ኢንስፔክተር አዳሙ መልካሙ፣ታላላቅ መምህራንና ደራሲያን፣ታራሚዎችና ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይም የመክፈቻ ንግግር በም/ኢኒስፔክተር በአቶ አዳሙ መልካሙ፤የዝግጅቱን አስፈላጊነት በተመለከተ በአቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ጥቅል ገለጻ ለታራሚው ተደርጓል።
በዝግጅቱ በተሳተፉ ታላቅ ሰው በአቶ ዮናታን መንክር ንባብ በማረሚያ ቤት በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ማረሚያ ቤት ሆናችሁ መጽሐፍ የምታነቡ ከሆነ ትፈታላችሁ ካላነበባችሁ የአእምሮ እስረኞች ነው የምትሆኑት እስትወጡ ሆናችሁ ለመውጣት መጽሐፍትን አንብቡ ሲሉ ደራሲ ገዛኸኝ ሀብቴ ደግሞ ማረሚያ ቤትን በምናብ መኖር በሚል ርዕሳቸው ማረሚያ ቤት ስትመጡ በምናባችሁ የምታስቡት ነገርና የምታገኙት ልዩ በመሆኑ ንባብ አንብቡ ለመለወጥ ያለን ግዜ እንድታሰላስሉት እናንተም ይህንን ግዜ እንደ ትምህርት ቆጥራችሁ በማንበብ አእምሯችሁን ጥመዱት መጥመድ ከቻላችሁ የምታስቡትን ጊዜ እንድታሰላስሉት ይረዳችኃል በማለት መክረዋል።
በሚዛን አማን ከተማ ማልምዳቸውን ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር ታርመው የወጡት የቀድሞው ታራሚ እጩ ዶ/ር አማረ ፈንታሁ የማረሚያ ቤት ልምዳቸውን ለታራሚው ሲያካፍሉ የዛኔ ለማንበብ ብዙ ፍላጎት ቢኖርም መጽሐፍ ማግኘት የሚችሉት በግዜው ትምህርት ላይ ላሉ ተማሪዎች ሲሆን የማንበብ ፍላጎታቸውን ከእርሳቸው ቀድመው ማረሚያው ከነበሩ ታራሚዎች እጅ ላይ የሚገኙ መጻሕፍትን በማሰባሰብ እንደሚያነቡና እንደሚያስነብቡ ተናግረው የአሁን ታራሚዎች እድሉ ስለተመቻቸላችሁ ልታነቡና ወደ ማህበረሰቡ ስትቀላቀሉ የበቃችሁ ልትሆኑ ይገባል በማለት ታለታራሚው ምክር ለግሰዋል።
በዝግጅቱም ታራሚዎች ይዘታቸው ጥልቅ የሆኑ መልዕክት አዘል የስነ ጽሐፍ ስራዎች ሲያቀርቡ የስነ ጽሑፍ ስራዎችን ላቀረቡና ከታራሚዎች መካከል ለተጠየቁ ጥያቄዎች መልስ ለመለሱ ተሳለሚዛን ከአገልግሎቱ የተዘጋጁ የመጽሐፍ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
ከአገልግሎቱ ለቤንች ሸኮ ዞን ለሚዛን አማን ከተማ ማረሚያ ቤት በይዘታቸው የተለያዩ እውቀት ዘርፍ ያላቸው በቁጥር ሦሥት መቶ መጽሐፍት አቶ ያሬድ ተፈራ ለማረሚያ ቤቱ ኃላፊ አስረክበዋል።
በመጨረሻም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ባህል፣ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ ተወካይ አቶ ወንድሙ ለማ በማጠቃለያ መልዕክታቸው ስዎችእነዚህ በሚገጥሙን መሰናክሎች መሰናክሎችን ለማጥፋት የሚረዳው መጽሐፍ በመሆኑ አንብቡ እንዲሁም የእደ ጥበብ ሙያዎችንም ተማሩ የተማራችኃቸው ሙያዎች ነገ ወደ ማህበረሰቡ ስትቀላቀሉ ለለውጣችሁ መሰረት ናቸው በማለት ታራሚውን መክረዋል።