የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር ማንበብ ዘላቂ መፍትሔ መሆኑን የሚያመላክት የንባብ ሳምንት ተከፈተ

የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር ማንበብ ዘላቂ መፍትሔ መሆኑን የሚያመላክት የንባብ ሳምንት ተከፈተ።

ከታሕሣሥ 15-18/2015 ዓ.ም የሚቆየውንና መጻሕፍት ለእውቀት ገበታ፤መዛግብትና የጽሑፍ ቅርሶች ለዘመን ትውስታ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የንባብ ሳምንት ፣ ቡክፌር፣የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ኤግዚቢሽን ዛሬ ታሕሣሥ 15 /2015 ዓ.ም በሚዛን አማን ከተማ ተከፍቷል።

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣ ቤንች ሸኮ ዞን እና ሚዛን አማን ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ በጋራ ያዘጋጀውን የንባብ ሳምንት ፣ ቡክፌር፣የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ኤግዚቢሽን መርሐ ግብር የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ቅዳሜ 15/2015 ዓ.ም የበርካታ ተፈጥሮ ሀብት ባለቤት በሆነችውና በርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተቻችለው በሚኖሩባት አዲሲቷ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ በሆነችው ሚዛን አማን ከተማ አከናውኗል።

በዝግጅቱም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ ጸጋዬ ማሞ፣ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ጉዳዮች ኃላፊ እጬ ዶ/ር ካሳሁን ሙላት፣የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም፣የደቡብ ምዕራብ ኢ/ያ ክ/መ/ባ/ቱ/ስፓርት ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ወንድሙ ለማ፣ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ መጻሕፍት ለእውቀት ገበታ፤መዛግብትና የጽሑፍ ቅርሶች ለዘመን ትውስታ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የንባብ ሳምንት ፣ ቡክፌር፣የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ኤግዚቢሽን ተከፈተ።

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣ ቤንች ሸኮ ዞን እና ሚዛን አማን ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ በጋራ ያዘጋጀውን የንባብ ሳምንት ፣ ቡክፌር፣የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ኤግዚቢሽን መርሐ ግብር የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ቅዳሜ 15/2015 ዓ.ም የበርካታ ተፈጥሮ ሀብት ባለቤት በሆነችውና በርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተቻችለው በሚኖሩባት አዲሲቷ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ በሆነችው ሚዛን አማን ከተማ አከናውኗል።

በዝግጅቱም የደቡብ ምዕራብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ ጸጋዬ ማሞ፣ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ጉዳዮች ኃላፊ እጬ ዶ/ር ካሳሁን ሙላት፣የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም፣የደቡብ ምዕራብ ኢ/ያ ክ/መ/ባ/ቱ/ስፓርት ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ወንድሙ ለማ፣ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ፣የሚመለከታቸው የአገልግሎቱ ባለሙያዎች፣አንጋፋና ጀማሪ ደራሲያንና ጥሪ የተደረገላቸው መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም የአካባቢው ማሕበረሰብ ተገኝተዋል።

ዝግጅቱም በዞኑ የባህል ቡድን ባህላዊ ጭፈራ ድምቆ ሲጀመር የዝግጅቱ ዓላማ የያዙ መልክቶች በሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ በአቶ ግሩም ተማም፤በሚዛን አማን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ጉዴዮች ኃላፊ በእጩ ዶ/ር ካሳሁን ሙላት፤በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ በአቶ ጸጋዬ ማሞ፤በክልሉ ባ/ቱ/ስፓርት ቢሮ ተወካይ በአቶ ወንድሙ ለማ እና በአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር በአቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ የንባብ አስፈላጊነትና ለሀገር እድገትም ሆነ ስልጣኔ መሰረት መሆኑን ያደጉ ሀገሮችን ምሳሌ በመስጠት መልዕክት ተላልፏል።

የመጽሐፍት ስጦታውንም በተመለከተ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ለተሳታፊው ሲገልጹ ሚዛን አማን ከተማ ለሚገኙ ለአምስት 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ለአምስት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ለአንድ የህዝብ ቤተ መጻሕፍት ቤት፣ለአንድ ወጣት ማዕከል እንዲሀም ለአንድ ማረሚያ ቤት በቁጥር /4230/አራት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ እና በብር 946,684/ዘጠኝ መቶ አርባ ስድስት ሺ ስድስት መቶ ሰማኒያ አራት ብር የፈጅ መበርከቱን ተናግረው አክለውም እነዚህ በስጦታ የተበረከቱ መጻሕፍቶችን የአብያተ መጻሕፍት ኃላፊዎችና ርዕሳነ መምህራን ቤተ መጻሕፍቱን መዝጋት ሳይሆን ተማሪዎች እንዲያነቡበት ወይም አገልግሎት እንዲሰጡ እንጂ ተዘግተው እንዳናገኛቸውና መጻሕፍቱም ተማሪዎቹ ተጠቅመዋቸው የቆሸሹ እንጂ አዲስ ሆነው እንዳናገኛቸው በማለት አሳስበዋል።

በመርሐ ግብሩም አንጋፋው ደራሲ ፋሲል መንግስቱ እና ደራሲ ገዛኸኝ ሀብቴ ንባብን በተመለከተ ተሞክሮ አካፍለዋል።

በመጨረሻም የመጻሕፍት አውደ ርዕይ እና በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ክልሉን ሊገልጹ የሚችሉ ከመዛግብት ክምችት የተወሰዱ መዛግብቶች እና ፎቶግራፎች እንዲሁም የጽሑፍ ቅርሶች ኤግዚቢሽን በአዘጋጆቹ የበላይ አመራር በይፋ ተከፍቷል።

Share this Post