ለተለያዩ የግል ሆስፒታሎችና ሜዲካል ላቦራቶሪዎች የነጻ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የሴ/ህ/ወ/ጉ/ዳይሬክቶሬት ለተለያዩ የግል ሆስፒታሎችና ሜዲካል ላቦራቶሪዎች የነጻ የጤና አገልግሎት በመስጠት ያለባቸውን ማህበራዊ ኃላፊነት እንዲወጡ ባቀረበዉ ጥሪ መሰረት ቤተዛታ ሆስፒታል ፣ ሳንቴ ሜዲካል ላብራቶሪና የኢትዮጵያ የኩላሊት ህመም ማህበር ለተቋሙ ሰራተኞች የነጻ አገልግሎት በመስጠት አብሮ መስራት እንደሚፈልጉና ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ በተግባር እንዳሳዩ ተጠቁሟል፡፡

የተቋሙ የሴ/ህ/ወ/ጉ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አገሬ መኰንን የስራ ክልሉ በዋናነት በእቅድ ይዞ ከሚተገብራቸው ተግባራት አንዱ የሆነውን የነጻ የጤና አገልግሎት እንደሆነ ተናግረው ይህንኑ እቅድም ሙሉ አድርጎ ለመተግበር በተያዘው በጀት ዓመት ክፍሉ በእቅዱ መሰረት በየዓመቱ ኖቬምበር 14 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የስኳር ህመም ቀን ምክንያት በማድረግ ቤተዛታ ሆስፒታል በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ለሚገኙ ስራተኞች በተለይም እውቀትን ለትውልድ እንዲደርስ ሲያገለግሉ ለኖሩ 100 አንጋፋ ሠራተኞች ነፃ የስኳር፣ የደም ግፊትና የምክር አገልግሎት እንደተሰጠ እና የኢትዮጵያ የኩላሊት ህመም ማህበር ከሳንቴ ሜዲካል ላብራቶሪ ጋር በመተባበር በርካታ ባለሙያዎችን በማሰማራትና የህክምና ቁሳቁሶችን በማምጣት ነፃ የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የኩላሊት ምርመራ ፣የስኳርና የደም ግፊት የምርመራ እንዲሁም የምክር አገልግሎት ለ110 ሠራተኞች በመስጠት አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡ በተሰጠው የጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ፣ የምርመራና የምክር አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ሠራተኞች ደስታቸውን በመግለጽ ቀጣይነት እንዲኖረውም አስተያየት ሰጥተዋል ፡፡

እንዲሁም የተቋሙ የሴ/ህ/ወ/ጉ/ዳ/ዳይሬክቶሬት የሆኑት ወ/ሮ አገሬ መኰንን የጤና ግንዛቤ፣ የምክር አገልግሎት እና ቅድመ ምርመራ በማሳደግ የቅድመ መከላከል ዘዴን በማስፋት ለህክምና የሚወጣ ወጪ በመቀነስና በማስቀረት ለሃገር ግንባታ ለማዋል ስራ የሚጠይቅ ወቅት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም በጤና እክል ምክንያት የሚደርስን በአምራች እና ገቢ አመንጪ ሃይል መመናመን የሚመጣን የቤተሰብ ብሎም የሃገር ድህነት መቀነስ ይቻላል፡፡ እንዲሁም እየተከናወኑ ባሉ የልማት ስራዎች ተሳታፊና ተጠቃሚም ማድረግ ይገባል፡፡ በማለት የህክምና አገልግሎቱን ላበረከቱ ተቋማት ላደረጉት በጎ ተግባር በተቋማችንና በሠራተኖቻችን ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ ዜጎች ያለምንም ልዩነት የትምህርት፣ የጤና የመኖሪያና የመሳሰሉት አገልግሎቶች ፍትሃዊ እና እኩል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ቢፈቅድም የጤና መድህን አገልግሎት አሰጣጥ አሁን ባለው አሰራር የመንግስት ሰራተኞችና ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው አገልግሎቱን እንዲያገኙ የሚፈቅድ ስላልሆነ የጤና ሚኒስቴር ለነገ ሳይል በያዝነው በጀት ዓመት በተጀመረው ዙር የምዝገባ መመሪያን በማስተካከል የመንግስት ሰራተኞች ከግል ድርጅት ያነሰ ክፍያ ሊያገኙ እንደሚችሉና ከሚሰሩበት መስሪያ ቤትም በስራ ላይ ከሚደርስ አደጋ ውጭ ምንም አይነት የጤና ሽፋን እና የጤና ወጭ የማተካኪያ ክፍያ ስለሌለ የመንግስት ሰራተኞች በስማቸው በመመዝገብ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማሻሻያ እንዲያደርግ በተቋማችን ሠራተኞች ስም የሚመለከተውን አካል ጠይቀዋል፡፡

Share this Post