የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ የመኖር መብቱ ተጠብቆ ሊኖር እንደሚገባ ተገለጸ

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና የቡድን መሪዎች የተገኙበት የጸረ ጾታዊ ጥቃት ቀን፣የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን እና ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር አዳራሽ አክብረዋል፡፡

በዝግጅቱም የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና አስፈጻሚ በአቶ አህመድ መሐመድ የመክፈቻ ንግግር እና መልእክት ሲተላለፍ ስራ አስፈጻሚውም በመልዕክታቸው የሰው ልጅ በሚገጥሙት የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ችግሮች በሚደርስበት ጉዳት መብቱ ተጠብቆለት ሰው በመሆኑ ብቻ በሰውነቱ የመኖር መብትና በጣም የተያያዙ ትልቁ ጉዳዮች ስለሆኑ እነዚህን ጉዳዮች አስበንበት እንድንሔድ እና በስራዎቻችን ውስጥ ሆነው እንድንገነዘባቸው የሚያስታውስ ቀን በመሆኑ በየቀኑ ልንሰራቸው የሚገባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ለማስታወስ እንደሆነ ተናግረው አክለውም እንደነዚህ ዓይነት ቀኖችን አስበን ስንውል የሚድያ ግባት ብቻ ለማድረግ በዓመት አንዴ ብቻ አስበን የምንለያይበት ሳይሆን በዕቅዶቻችን ላይ በማካተት አቅደን ወደተግባር የምንገባበት ሊሆን እንደሚገባል ብለዋል፡፡

በዕለቱም ቀኖቹን በማስመልከት በተለያዩ የዘርፉ ባለሙያዎች የተዘጋጁ የመወያያ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ጸረ ጾታዊ ጥቃት ቀንን በተመለከተ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዘዳንት በወ/ሮ አሸነፈች አበበ የሴቶችን መብት ጥሰትን የሚመለከቱ የህግ ማዕቀፎች ተግዳሮቶች እና መፍትሔዎች ላይ ጽሑፍ ሲቀርብ፤ስለመጤ ልማዳዊ ድርጊቶችና ጾታዊ ጥቃትን በተመለከተ በመ/ር ደረጀ ነጋሽ፤በኤች አይቪ ኤድስ ላይ በሲስተር ገነት ማሞ ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ፌደሬሽን በወ/ሮ እጸገነት አሳዬ አጭር የመወያያ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ሲደረግባቸው እያንዳንዱን ቀኑን የሚመለከቱ መልዕክት አዘል ግጥሞች በብሔራዊ ቲያትር ባለሙያዎች ለታዳሚው ቀርበዋል፡፡

 

Share this Post