“ ሙስናን መታገል በተግባር ! ” በሚል መሪ ቃል የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በየዓመቱ እንደ ሀገር ኀዳር 30 የሚከበረውን የጸረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ መልዕክት አዘል ዝግጅቶች በድምቀት አከበረ፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ተኛ ጊዜ / 19th International Anti-Corruption Day December 9/2022 በሀገራችን ኢትዮጵያ ለ18ተኛ ጊዜ “ ሙስናን መታገል በተግባር ! ” / Fighting corruption in action/ በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የጸረ-ሙስና ቀንን ኀዳር 28 / 2015 ዓ.ም በተቋሙ አክብሯል።
በዕለቱም የተቋሙን ዋና ዳይሬክተር በመወከል አቶ አብነት አበራ እለቱን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስነ ምግባር መከታተያ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ክንፈ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ላይ የመወያያ ጽሑፍ አቅርበው እንደ ሀገርም እንደ ተቋምም ያሉ ነጥቦች ላይ በተሳታፊዎች ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት ሲደረግ የእለቱን ጉዳይ በተመለከተ መልዕክት አዘል ወግ በወሪ/ት ፍሬዘር ዘውዴ ሲቀርብ ከተቋሙ ከተለያዩ ክፍሎች በተውጣጡ አምስት ባለሙያዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሒዷል፡፡
በጥያቄና መልስ ውድድሩ ተሳትፈው ከ1ኛ እስከ 3ተኛ ደረጃ በመውጣት ነጥብ ላስመዘገቡት ለሦሥቱ ተሳታፊዎች የመፅሐፍት ሽልማት ሲበረከት ለጥያቄና መልስ ውድድር ተሳታፊዎች ቀርበው መልስ ያላገኙ ጥያቄዎችን ለመለሱ ተሳታፊዎች የሞባይል ካርድ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በመጨረሻም የበዓሉን ዓላማ አስመልክቶ ያነጋገርናቸው በተቋሙ የሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና መከታተያ ቡድን ከፍተኛ ባለሙያ መምህር ካሳዬ ስሜ እንደተናገሩት ዓለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ለሚከበረው በዓል የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች የሙስንና ብልሹ አሠራርን አስከፊ ገጽታ እንዲገነዘቡ በማድረግ በተቋሙ ብልሹ አሠራርና ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው ትግል ንቁ ተሳትፎ እንዲኖር ለማስቻል ነው ብለዋል፡፡

Share this Post