የኩላሊት ቅድመ ምርመራ ተደረገ

የኩላሊት ቅድመ ምርመራ ተደረገ፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ሰራተኞች ዛሬ ሕዳር 14/2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ የኩላሊት ሕመም ማህበር በተደረገ ድጋፍ የኩላሊት ህክምና ቅድመ ምርመራና ሌሎች ለበሽታው አስጊ የሚሆኑ ሕክምናዎችን ያለምንም ክፍያ ምርመራ አድረጉ፡፡

የኢትዮጵያ የኩላሊት ሕመም ማህበር ለትርፍ የማይሰራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (Non Profit Non Governmental) እንደሆነና የኩላሊት ሕመም ማህበር የተቋቋመው በኢትዮጵያውያን ግለሰቦች እና በኩላሊት ሕክምና ባለሙያዎች፤ የኩላሊት ሕመምተኞችና ሌሎች ግለሰቦች ሲሆን እውቅናውንም በተመለከተ ባህበሩ በፍትህ ሚኒስቴር የተመዘገበ ህጋዊ አካል ሲሆን በየጊዜውም ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራና የፋይናንስ ሪፖርትም የሚያቀርብ እንደሆነና ማህበሩ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር እና ከጤና ጋር ከሚሰሩ አካላት ጋር በቅርበትም እንደሚሰራ ተጠቁሞዋል፡፡

Share this Post