በሰነድ ስራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከጥቅምት 9-18/2015 ዓ.ም ሲሰጥ የነበረውን ተከታታይነት ያለው የሰነድ ስራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር ስልጠና አጠናቋል፡፡
ስልጠናው ከተለያዩ የክልል ከተሞች እና ከዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከፌደራል የመንግስት ተቋማት ለተውጣጡ 55 /ሃምሳ አምስት/ የሪከርድ ማህደር ክፍል ባለሙያዎች የተሰጠ እንደነበር የአገልግሎቱ የአብያተ መዛግብትና አብያተ መጻሕፍት ጥናትና ምርምር ስልጠና ዳይሬክቶሬት ጠቁሟል፡፡
ስልጠናው ያተኮረው በሰነድ ስራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር ዙሪያ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡