ለሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ ሥልጠና ተሰጠ

በባህል እና በስፖርት ልማት ዘርፍ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ዙሪያ ለሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በአዲሱ አደረጃጀት በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 የተሰጡ ተግባር እና ኃላፊነቶችን ለመወጣት ያስቀመጣቸው ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲ ጉዳዮች፣ አሠራሮች እና የ10 ዓመቱን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ልማት ዕቅድ ዙሪያ ለሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች በማስተዋወቅ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ዓላማ ያደረገ የግንዛቤ መፍጠሪያ ሥልጠና መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ተሰጥቷል፡፡

ሥልጠናውን መልዕክት በማስተላለፍ ያስጀመሩት አቶ አለማየሁ ጌታቸው የሚኒስቴሩ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ በዕለቱ መልዕክታቸውም የአንድ አገር ዋነኛ ሀብት መረጃ በመሆኑ መረጃዎች ተደራሽ ሲሆኑ የወጠናቸው ዕቅዶች ውጤታማነት በአጭር ጊዜ ማረጋገጥ ይቻላል። በመሆኑም እቅዶቻችን ውጤታማ መሆን እንዲችሉ የኮሙኒኬሽን እና የብዙሃን መገናኛ ባለሙያዎች በተቀናጀ አግባብ መስራት ሲችሉ ያሉንን የመረጃ ሀብቶች በሚገባ የማስተዋወቅ የህብረተሰብን ግንዛቤ ከማዳበር አንጻር ከፍ ያለና ላቅ ያለ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰው፤ ተሳታፊዎች በቆይታቸው የተቋሙን አሠራሮች ተረድተው የተቋሙን ተግባራት በማስተዋወቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ በማሳሰብ መርሐ ግብሩ ተጀምሮ ስልጠናውም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ተሰጥቶ ለሚድያውና ለኮሙኒኬተሮች ተቋማት ከተቋቋሙለት አንጻር ስራዎችን እንዴት ለማህበረሰቡ ማድረስ እንደሚቻልና የታቀዱ እቅዶች ከአፈጻጸማቸው እንዴት እንደተለኩ የሚያስረዱ መረጃዎችን ከማድረስ አንጻር ሚድያዎች ስለሚጠበቅባቸው ድርሻ ግንዛቤ በማስጨበጥ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

Share this Post