ተቋሙ በወርሀ መስከረም ታሪካዊ ገጸ በረከትን ተረከበ።

መስከረም 5/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ሁለት ጥንታዊ የብራና መጻሕፍትን በኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን በተቋሙ የመዛግብት አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የዋና ዳይሬክተር ተወካይ በአቶ ሰለሞን ጠና ተረክቧል።
እነዚህ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍትን በባለቤትነት ይዘው የነበሩት አሁን በህይወት የሌሉት ሚስተር ጄነራል ዋይነር ነበሩ። ህይወታቸው ከማለፉ በፊት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ፍቃዳቸውን ለፕሮፌሰር ስቲቭ ዴላማተር እና ቡድናቸው መግለጻቸውን በማክበር ባለቤታቸው ወ/ሮ ባርባራ ዋይነር ያለምንም ክፍያ አስረክበዋል።
ተቋሙ የተረከባቸው ሁለት ጥንታዊ የብራና
መጻሕፍት አንደኛው ዳዊት የብራና መጽሐፍ የራስ መንገሻ ስዩም የነበረ ሦስት የዘር ሐረግ ያለው ሲሆን ሁለተኛው ዳዊት የብራና መጽሐፍ የጽህፈት ሚኒስቴር ንብረት መሆኑ የተመለከተበት ነው።
በዕለቱ በተደረገው ርክክብ በአጠቃላይ 17 የጥንታዊ ብራና መጻሕፍት ለሰባት /7ተቋማት እንደ የጽሑፍ ቅርሱ አይነት በተለዩት እና በወ/ሮ ባርባራ በተላለፉት አግባብ መሠረት ተለይተው ተረክበዋል።
በዚህ መርሐ ግብር  የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረ/ፕ አበባው አያሌው ፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ሽኩር እና ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት የጽሑፍ ቅርሶቹ እንዲመለሱ ለሰሩት ለፕሮፌሰር ስቲቭ ዴላማርተርና የምርምር ቡድናቸው ምስጋና አቅርበዋል።
ይህ ልዩ የርክክብ ሥነሥርዓት በተፈጸመበት መድረክ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም፣ልዕልት ማርያም ሰና፣የፕሮፌሰር ስቲቭ ቡድን፣የዘርፉ ምሁራኖች እንዲሁም በሰዓሊው ለብሔራዊ ሙዝዬም ለመበርከት በ19 98 ዓ.ም ተሰርቶ  የተዘጋጀ የራሳቸውን የፖርትሬት ምስል ለባለስልጣን ተቋሙ ያስረከቡት አርቲስት አብራር አብዶ ተገኝተዋል።

 

Share this Post