የኢትዮጵያ ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል የኅብር ቀን ተከበረ።

የኢትዮጵያ ማንሰራራት!በሚል መሪ ቃል የኅብር ቀን በኪነ-ጥበብ ዝግጅት ታጅቦ ተከብሮ ውሏል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ ፀጋዬ ማሞ
ኅብረ ብሔራዊነት የኢትዮጵያ ማንቂያ እና ጥንካሬ በመሆኑ ልዩነቶችን አጥብቦ በአንድነት መቆም እንደሚገባ ገልፀዋል።
ማንነታችን የጽናታችን ሚስጥር ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በአዲሱ ዓመት ከግጭት እና ከፋፋይ አስተሳሰቦች በመውጣት የመደመር፣የመቻቻል፣የመደጋገፍ እና የፍቅር መንፈስ ሊጎላ ይገባልም ብለዋል።
ቀኑ በግጥም፣በሙዚቃ፣በዳንስ እና በሰርከስ ትርኢቶች ታጅቦ የኢትዮጵያን ኅብረ-ብሔራዊነት እና አብሮነት በሚያንጸባርቅ መልኩ ተከብሯል።
በመርሐ ግብሩ አዲሱ ዓመት የእውነተኛ ወንድማማችነት፣የእህትማማችነት፣የሰላም፣የፍቅር እና የጋራ እድገት ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞት ተገልጿል።
በዝግጅቱ  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች ቴአትር፣ የወጣቶች እና ህጻናት ቴአትር ቤት እንዲሁም የሰርከስ ቡድኖች ለዝግጅቱ ስኬት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና ቀርቦላቸዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴ፣ከኢፌዴሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት፣ ከሰላም ሚኒስቴር፣ ከፍትህ ሚኒስቴር፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከተጠሪ ተቋማት ጋር በትብብር ዕለቱ ተከብሮ ውሏል።

Share this Post