ሁለቱ አንጋፋ ተቋማት የልምድ ልውውጥ አደረጉ።

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት የልምድ ልውውጡን በተመለከተ እነዚህ ሁለት ተቋማት ሁለቱም እንደሀገር አንጋፋ ተቋማት ቢሆኑም የህትመት ውጤትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቀዳሚነቱን ቢይዝም መረጃን ሰንዶ ለትውልድ ከማስቀመጥ አንጻር አገልግሎቱ የቀደመ ሲሆን አዲስ ዘመን ጋዜጣንም በተመለከተ በየእትሙ ሦሥት ሦሥት ኮፒ በተቋሙ እንደሚገኝ ተናግረው።
ማተም ይቀድማል ከማስነበብ ያሉት አቶ ሠርፀ ዛሬ ያገናኘን ደግሞ የሉንን መረጃዎች ዲጅታላይዝድ የማድረጉን ስራ አገልግሎቱ ቀድሞ ወደተግባር መግባቱን አመላክተዋል።
ብዙ ሰው የሚፈልገው አገልግሎት ያለው የሕግ ክምችት ላይ ጋዛጣ ሲሆን በጣም ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት እንዳለና የታሪክ ዋና ጉዳይ ሆነው ቁጭ እንደሚሉና የየዘርፉ ጥናት አጥኚዎች ለጥናታቸው ተወዳጅ የሚሆኑት ጋዜጣ ሲሆን ያም ደግሞ የእናንተ ምርት ነው ያም በመሆኑ በጣም እንኮራበታለን ብለዋል።
አክለውም ይህንን ዲጅታላይዝ በጋራ ማድረግ እንደሚጠበቅና ይህንንም ደግሞ ወደ አገልግሎት ማድረስ ህያው ነው የሚሆነው ዲጂታል 2030 አንዱ ግብ እርሱ ስለሆነ እርሱን ማድረግ እና ሌሎችንም ሃሳቦች የምንወያይበትና ልምድ የምንለዋወጥበት ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መሳፍንት ተፈራ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከታተሙ ጋዜጦች በተጨማሪ መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችና ድረ-ገጾች ላይ ሰፊ የዲጂታል ሚዲያ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ድርጅቱ በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ መረጃዎችን «ጋዜጣ ፕላስ / Gazette Plus» በሚል ስያሜ ለሕዝብ እያደረሰ እንደሚገኝ እና ከአገልግሎቱ የቀደመው ይሄንኑ ፕላት ፎርም እንደሆነ ተናግረዋል።
የስራ ግንኙነትን በተመለከተ አቶ መሳፍንት ሲገልጹ ተቋማት እድሜ እኩዮች ሲሆኑ መደማመጥም ይኖራል። በእድሜያቸው አነስተኛ ከሆኑ ተቋማት ጋር ስራዎቻችንን ለመሥራት በምናደርገው ግንኙነት የሚፈጠሩ አለመግባባቶች አይኖሩም በማለትም ተናግረዋል።
የልምድ ልውውጡ በዘመን እኩል የሆኑ ሁለቱ ተቋማቶች አዳዲስ ልምድ በመለዋወጥ ያሉ መረጃዎችን ለትውልድ ለማቆየት ማስቻል ሲሆን ከእንደዚህ ዓይነት በዕድሜ እኩዮች ከሆኑ ተቋማት ጋር የምንሰራው ስራ ዕድሜያቸው አነስተኛ ከሆኑ ተቋማት ጋር ስራዎቻችንን ስንሰራ በምናደርገው ግንኙነት የሚፈጠሩ አለመግባባቶች እንደማኖሩም ተናግረዋል።
አገልግሎቱ በተቋሙ የሚገኙ የሀገር ሀብቶችን ዲጂታላይዜ ወደ ማድረግ ስለገባ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
ድርጅቱ የሚያሳትማቸውን እንደ አዲስ ዘመን እና ኤራልድ ያሉ ጋዜጣዎችን፣ መጽሔቶችን እንዲሁም ሌሎች ዲጅታል መደረግ የሚፈልጉትና ለትውልድ ጠብቆ ከማቆየት አንጻር የዛሬ ልምድ ልውውጥ ጥሩ አጋጣሚ እንደሚፈጥር አመላክተው ከዚህ ሀገራዊ ተቋም እንዲሁም ከዘመን እኩያ፤ ከስራም ተመሳሳይነት ካለው ተቋም ጋር አብሮ መስራት ለሁለቱም ተቋማት ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነም ተናግረዋል።
የዚህ ዓይነቱ የሥራ ግንኙነት የሚታዩ የመረጃ አያያዝ ችግሮቻችንን ከመፍታታቸው ባለፈ መረጃዎች ዲጅታላይዝ ሲደረጉ ከድግግሞሽ የመዳን፣ለመረጃ ፈላጊዎች መረጃዎችን በሚፈልጉት ቦታ ሆነው መረጃዎችን ማግኘት እንዲችሉ የሚያግዝ እና መረጃ ፈላጊዎች መረጃዎችን በነጻነት ለሚፈልጉት ዓላማ መጠቀም እንዲችሉ እንደሚረዳ ተጠቁሟል።
በመጨረሻም የአገልግሎቱ የሙያው ባለቤቶች ዲጅታላይዝድ የሚደረጉ ሰነዶችም ሆኑ የድምጽ ቅጅዎች ቀድመው የመረጣና ልየታ ስራ የሚፈልጉ መሆናቸውንና ተቋሙ የድጅታላይዝ ስራዎችን በሚያከናውንበት ወቅት የተገኙ ጥቅሞችንና የገጠሙትን ተግዳሮቶች ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚው ለአቶ መሳፍንትና ከእሳቸው ጋር ለመጡ ኮሚቴዎች በስፋት የማስረዳት እና የተቋሙን የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች በባለሙያዎች ገለጻ እየተደረገ እንዲጎበኙ ተደርጓል።

 

Share this Post