አርካይቭን ዲጅታላይዝ ማድረግ የሚያስችል ስምምነት ሠነድ ተፈረመ
ነሐሴ 6/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከጃፖን የሎካል ሚድያ ጋር በተቋሙ የሚገኙ የጽሑፍ ቅርሶችን ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ዲጅታላይዝድ ለማድረግ የቅድመ ሥራ ውል መግባቢያ ስምምነት ሠነድ ተፈራርሟል፡፡
በመግባቢያ ሠነዱ መፈራረሚያ ላይ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት እንደተናገሩት ኢትዮጵያና ጃፖን የቆየ የወንድማማች ግንኙነት እንዳለን ብዙ ማሳያዎች ሲኖሩ የጃፖንን ስልጣኔ ለሀገራችን ለማስተዋወቅ ትልቅ ስራን የሰሩት ታላቅ የአገራችን ሰው ከበደ ሚካኤል ይሄ አሁን የመጣችሁበትንና የአገርን ሀብቶ ሠንዶ የያዘውን ግዙፍ ተቋም እንደመሩት ተናግረዋል።
ከጃፖን ጋር ግንኙነታችን የባህል ጥቅም እንደሚሆንም እርግጠኛ እንደሆኑም ገልጸው
በዚህ በ83 ዓመታት ውስጥ የሰበሰብናቸው የተወሰኑ የጽሑፍ ቅርሶች በግምት ከሁለት ሺህ እስከ አንድ ሺህ ዘመን ያስቆጠሩ እንደሆኑ ጠቁመው ዛሬ ከእናንተ ጋር ውል የምንገባው የአርካይቭ ዲጅታላይዝ ስምምነት አንዱ እና ዋነኛው በተቋማችን የሚገኙ የጽሑፍ ቅርሶች ሲሆኑ በሁለተኛነት በመዛግብት ደረጃ ያሉንን ከግለሰቦች፣ ከተቋማት የተሰበሰቡ መረጃዎቻችንን ናቸው ብለዋል።
ይሄ አገራዊ ተቋም ህትመት መታተም ከጀመረበት ዘመን አንስቶ የታተሙ መጽሔቶች፣ ጋዜጣዎች፣ መጻሕፍቶች፣ ወዘተ የሚሰበስብ ብቸኛም ተቋም እንደሆነም ገልጸውላቸዋል።
ይሄ ዛሬ እዚህ ደረጃ የደረሰ የሥራ ውል ስምምነት በተለያየ ግዜ ለስድስት ያህል ጊዜያት ውይይት የተደረገበት እንደሆነና ይህንኑ መረጃዎችን ዲጅታላይዝ የማድረጉ ስራ አጣዳፊነትን የሚፈልግ መሆኑንም ኃላፊው በድጋሚ አስገንዝበዋል።
የጃፖን Local media Labs CEo Mr. Kiyohide Ushijima ይሄንን ስራ ሲሰሩ ጃይካ ስፖንሰር እንደሚያደርገው ተናግረው ስራው ሲሰራ የኢትዮጵያን የጽሑፍ ሐብቶች በጃፓን የሰርቬይ ሲስተም ውስጥ ለማስገባት ሳይሆን ጃፖን ውስጥ የተደረገውን የጃፓን ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ ላይ ለኢትዮጵያ አርካይቮች /የጽሑፍ ቅርሶች እንድንጠቀምበት እና ቴክኖሎጂውን ለማስተዋወቅ ሲሆን የሀገርን ጥቅም ያስጠበቀ ስራ በጥንቃቄ እንደሚሰራ እና ጊዜውም ከ2027_2029 G.C የሁለት ዓመት እንደሆነና ስራው ካላለቀም አራዝመው መስራት እንደሚፈልጉም ጠቁመው ከሁለቱ የስምምነት ዓመታት የመጀመሪያው አንዱ ዓመት የጥናት ግዜ እንደሆነ አመላክተው በጃይካ የታቀደ ፕሮጀክት እንደሆነም ገልጸዋል።
ከተቋሙ የማኔጅመንት አባላት እነኚ የአገር ሀብቶች ዲጅታላይዝድ በሚደረጉበት ወቅት ስጋት ይሆናሉ የሚሏቸውን ሃሳቦች አንስተው በMr. Kiyohide Ushijima ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
ስራውን ለመስራት ሰርቨር ከሚሰሩት ወይም ከኢትዮጵያ ቴሌኮም ጋር ከዛሬ ጀምሮ እንደሚነጋገሩ፤ለጃፖን መንግስት ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተጻፈ ደብዳቤ እንደሚፈልጉም Mr. Kiyohide Ushijima እና አባላቱ ለተቋሙ የማኔጅመኑት አባላት ሃሳብ አቅርበዋል።
ከውል ስምምነቱ በተጨማሪ A proposal For Building aDigital Archive System በሚል ርዕስ በሎካል ሚድያው የተዘጋጀ ፕሮፖዛል ለውይይት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ዋና ዳይሬክተሩ አባላቱ ለስራው መሳካት እና ስለ ተቋሙ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተቋሙን እንዲጎበኙ ጋብዘዋቸዋል።
በመጨረሻም የመግባቢያ የውል ስምምነቱን አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት እና Mr. Kiyohide Ushijima በጋራ ተፈራርመው ተቋሙ ያዘጋጀውን ስጦታ አበርክተውላቸው ዝግጅቱ ተጠናቋል።