መረጃዎችን በሜታዳታ በጥራት እና በትክክል እንድያስገቡ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

በተቋሙ በሚገኙ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት የሜታዳታ አመዘጋገብ ዙሪያ በዘርፉ እየሰሩ ለሚገኙ ባለሙያዎች ሦሥተኛ ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሠጠ።
ሰኔ 7/2018ዓ.ም አዳማ
ጥራት ያለው ሜታዳታ የተሻለ መዳረሻ፣የተሻለ ጥበቃ እና የተሻለ ዕውቀት ማጋራትን ያረጋግጣል ተባለ።
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በተቋሙ የሚገኙ የሀገር መረጃዎችን ጥራት ያለው ሜታዳታ ውስጥ በማስገባት ሰዎች ወደ ተቋሙ መምጣት ሳይጠበቅባቸው መረጃ ማግኘት እንዲችሉ በዘርፉ ለሚሰሩ ባለሙያዎች አንድ ዓይነት አረዳድ እንዲኖራቸው የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በግንዛቤ ማስጨበጫው በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ሥራ አመራር አቶ አብነት አበራ ይሄ ስልጠና ለሦሥተኛ ዙር እንዲሰጥ የተፈለገው በዘርፉ የሚሰሩ ባለሙያዎች የተለያየ እና የተዘበራረቀ የመረጃ አሞላል  እንዳላቸው በመገንዘብ የተዘጋጀ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንደሆነ ተናግረው  ይሄንን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ካገኙ በኃላ ስራውን የሚሰሩ ባለሙያዎች አንድ ዓይነት አረዳድ ኖሯቸው በዲጅታል2030 ዓ.ም በመንግስት ደረጃ ለተያዘው ዲጂታል ኢትዮጵያ ትኩረት የተሰጠውን እንደ እኛ ተቋም የሚገኙ የሀገር መረጃዎች ሜታዳታ በትክክል መሙላት እንዲችሉ እና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት እንደሚያስችላቸው ጠቁመዋል።
ጥራቱን የጠበቀና ግልጽ የሆነ ሜታዳታ ካልያዝን እንደ ተቋም ከተመረጡ ተቋሞች ውስጥ ላንገባ ስለምንችል ይሄንን ስልጠና በማግኘታችሁ መረጃውን ወጥ በሆነ መልኩ መያዝ እንድንችልና ጥራት ያለው ሜታዳታ ተመዝግቦ መረጃው ለመረጃ ፈላጊዎች ግልጽ ሆኖ መቀመጥ እንዲቻል ለዘርፉ ባለሙያዎች እየተሰጠ የሚገኘው የግንዛቤ ማስጨበጫው ስልጠና ወቅቱን ያማከለ እንደሆነም ተናግረዋል።
ይህንን ጊዜውን የዋጀ ስልጠና አዘጋጅቶ እየሰጠ የሚገኘው የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ግዛው ዋቅጅራ በግንዛቤ ማስጨበጫው የሜታዳታ ምንነት፣በቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ መጻሕፍት፣ሰነዶች፣ ፎቶ ግራፎች፣ካርዶች፣ዲጅታል ፋይሎች እና ሌሎች ሀብቶች ለመግለጽ ለማደራጀት፣ ለሚፈልግ እና ለሚጠብቅ የሚያገለግል የተዋቀረ መረጃ መሆኑን
ሲያስገነዝቡ የሜታዳታ አስፈላጊነትንም የመረጃ ፍለጋን እንደሚያሻሽል፣ የስብስብ አስተዳደርን እንደሚያቀላጥፍ፣ ዲጅታል ጥበቃንም እንደሚያጠናክር፣የመረጃ ልውውጥንም እንደሚያሳልጥ ጠቁመው የሚታዩ ተግዳሮቶችን በተመለከተ የባለሙያ እጥረት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ውስንነት፣የሜታዳታ ቁጥጥር አለመዘርጋት፣መመዘኛ /መስፈርት/አለመኖር፣የመረጃ ጥራት ችግርም እንደሚገጥም ዳታ ጀምሮ የማቋረጥ ነገርም እንደሚኖር ተናግረዋል።
ስራ አስፈጻሚው ባቀረቡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሑፋቸው በማጠቃለያነት ሜታዳታ በቤተ መዛግብትና ቤተመጻሕፍት ውስጥ የመረጃ አስተዳደር ፍለጋ፣ጥበቃ እና የመረጃ ልውውጥ መሠረታዊ መሣሪያ እንደሆነም ጠቁመው አክለውም ሜታዳታ በመረጃ አስተዳደር ተደራሽነት እና ጥበቃ መሠረት መሆኑንም ገልጸዋል።
በመቀጠል በአብያተ መጻሕፍት መረጃ ሃብቶች መሪ ስራ አስፈጻሚ የማደራጃ ዴስክ ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ሂሩት ካሳ ILARMs Essentials: Standard Cataloging Training እና የመዛግብት ማደራጃ ዴስክ ኃላፊ በአቶ አብይ ብሩክ ደግሞ በመዛግብት አደረጃጀት ከምዘና መረጣ ጅምሮ፣ አደረጃጀቱን፣ የመግለጫዎች አዘገጃጀቱን፣ ለመዛግብቱ እንክብካቤና ጥበቃ በማድረግ እንዴት አገልግሎት
ላይ እንደሚውሉ እንዲሁም መዛግብት በ Integrated Library, Archives and Records Management System (ILARMS) Software እንዴት መዛግብቱ እንደሚደራጁ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
በቀረቡት ሰነዶች ላይ ጥያቄ፣ሃሳብ አስተያየት ሲቀርብ ሰልጣኞቹ
ስልጠናው ከበፊቱ በተሻለ እውቀት ኖሯቸው እንዲሰሩ በባለሙያዎች በታገዝ ዳታ እንዲያስገቡ ልምምድ ሲያደርጉ፤ከዚህ ቀደም በእቅድ ተለክቶ የተሰጣቸውን ዳታ የማስገባት ስራም በተቀመጠው እቅድ መሰረት አጠናክረው እንዲሰሩ ስራውን ከሚከታተሉ ሥራ አስፈጻሚዎች መልዕክት ሲተላለፍ በስልጠናው
የዲጂታላይዝድ ባለሙያዎችም መሳተፍ እንደነበረባቸው ተመላክቷል።
ስልጠናውን ለሰራተኞቹ ያመቻቸው የተቋሙ የሰው ሀብት አስተዳደር እና ብቃት  የሥራ ክፍልም ስልጠናዎች መዘጋጀት ያለባቸው ከባለሙያው የአቅም ክፍተት በመነሳት እንደሆነ ዛሬ ከነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መረዳት እንደተቻለ ተጠቁሟል።

Share this Post