“እንገናኝ እንሰናኝ!”የሠራተኞች የሰኞ ንጋት መድረክ ሊጀመር ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ሠራተኞች የሰኞ ንጋት መድረክ የምክር ሃሳብ በየኹለት ሳምንት በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ስላሴ አዳራሽ ከግንቦት 3/2018ዓ.ም ጀምሮ መካሔድ ይጀምራል፡፡

የዚሁ የምክር ሃሳብ አመንጪው የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት የእንደነዚህ ዓይነት የምክር ሃሳብ መድረክ መዘጋጀቱ በማንኛውም ተቋም ውስጥ የሠራተኛው የሥነ ልቦና ዝግጁነት፣ የቡድን ስሜት እና የመቀራረብ ባህል ተቋማዊ ውጤታማነት ወሳኝ ሚና እንዳለው እና የተቋሙም ሠራተኞች የዕለት ተዕለት የሥራ ጫናን በመቀነስ፣እርስ በእርስ በመተዋወቅ፣ልምድ በመለዋወጥ እንዲሁም የግል ሕይወታቸውን የሚያበለጽጉ ክህሎቶችን እንዲቀስሙ የሚያስችል መሆኑን ባዘጋጁት ፕሮፖዛል መግቢያ አስፍረዋል፡፡

የዚህ ምክረ ሃሳብ ዓላማዎች፡-

የሠራተኞችን እና የማኔጅመንቱን ግንኙነት ለማጠናከር፤

 የተቋሙን ሠራተኞች የቤተሰባዊነት ስሜት ለማጠናከር፤

የግል ሕይወት ማነቃቃት (Motivation) እና የዕውቀት ሽግግር መድረክ ለመፍጠር፤

 በየ15 ቀኑ የምትመጣውን ሰኞ ለሠራተኛው በናፍቆት የምትጠበቅ በማድረግ አዎንታዊ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡

“እንገናኝ እንሰናኝ!” መድረክ የሠራኞችን የሥራ ተነሳሽነት ከመጨመሩም በላይ ተቋሙን እንደ አንድ ቤተሰብ የሚያስተሳስር ወሳኝ መድረክ ሊሆን እንደሚችል ታምኖበት የተዘጋጀ የምክር ሃሳብ ፕሮፖዛል ነው፡፡

ይህ ዓይነቱ የምክር ሃሳብ በከተማ ደረጃ በተሞከሩ እና ውጤታማነታቸው በተረጋገጡ መድረኮች ላይ የተመሰረተ የመድረክ ሃሳብ በመኾኑ በተቋችንም ተመሣሣይ ውጤት እንደሚያመጣ ይታመናል፡፡

በዚህ መልክ ቤተሰብአዊ ትሥሥርን ፈጥሮ ተቋሙን ከመለወጥ አንጻር ሥራዎችን ለማሳካት የጀመረ፤ ከሰራንበትም እንደ ፌደራል ተቋም የመጀመሪያው ያደርገናል፡፡

Share this Post