ብቻችንን እየሮጥን ነው ወይስ የሀገርን ትልቁን ርዕይ ለማሳካት እየሮጥን ነው? የሚለው በትኩረት ሊታይ እንደሚገባ ተገለጸ::

13/08/2018 አዲስ አበባ

የተከናወኑ ተግባራት የተቋሙን ግብ ማሳካታቸውን የሚፈትሽና ያልተከናወኑ ተግባራት ደግሞ በቀሩት ጥቂት ወራት ለመፈጸም የሚያስችል የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀረበ::

መሪ ስራ አስፈጻሚ ክፍሎች እያንዳንዳቸው ያከናወኗቸውን ተግባራትና ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች በጥልቀት ማቅረባቸው  ሪፖርቱን በአቀራረብ አካሄድና ይዘት ከቀድሞው የተሻለ እንደሚያደርገው ተገልጿል::

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት በንግግራቸው በየስራ ክፍሉ በተከናወኑ ተግባራት ብቻችንን እየሮጥን ነው ወይስ የሀገርን ትልቁን ርዕይ ለማሳካት እየሮጥን ነው? የሚለው በትኩረት ሊታይ እንደሚገባ ገልጸው

በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚገኙ ሰነዶች

በብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በሚገኙ የኢትዮጵያን የ50 ዓመታት የፓርቲ ታሪክ የሚያሳዩ ሰነዶች ላይ የተሰራው የዲጂታይዜሽን፣ የምዝና፣ የመረጣና የውገዳ ስራ

የቤተመጻሕፍት፣ የሰነድና የመዛግብት አስተዳደር ሙያዎቸ ላይ በሀገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚሰጡ ስልጠናዎቸ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ለሀገር ባላቸው ፋይዳ ማሳያ ከሆኑት መካከል ጥቂቶቹ እንደሆኑ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በግዥና በአዋጅ ከተሰባሰቡ በርካታ የመረጃ ሀብቶች በተጨማሪ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት የትውስታ ተቋም (Memory institution) መሆኑን በጉልህ የሚያሳይ  የፊት አውራሪ አመዴ ለማ ፣ የፕ/ር ተወልደ ገ/እግዚአብሔርና የአቶ ያየህይራድ አላምረው የግል ስብስቦች ባለፉት ዘጠኝ ወራት በስጦታ ወደ ተቋሙ ከተዛወሩ የመረጃ ሀብቶች መካከል እንደሆኑ ፣ የአቡነ ገሪማ ወንጌልን እና የሐረር የባቡር ዝርጋታ ዶክመንትን በአለም የጽሑፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ የተሄደው ረጅም ርቀት በቀረው ሩብ ዓመት እንድሚጠናቀቅ በቀረበው ሪፖርት  ተመላክቷል።

የቀሩ ያልተከናወኑ ተግባራትን በመጨረሻው ሩብ ዓመት በቁርጠኝነት፣ በዕለት ተዕለት ትጋት እና ፈጠራ በተሞላው የስራ አፈጻጸም ሊጠናቀቅ እንደሚገባው የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት አሳስበዋል።

Share this Post