ትኩረቱን አንባቢ ትውልድን ለመቅረጽ ታዋቂ ሰዎች እና የንባብ ተሞክሯቸውን የሚያካፍሉ ደራሲያን
ትኩረቱን አንባቢ ትውልድን ለመቅረጽ ታዋቂ ሰዎች እና የንባብ ተሞክሯቸውን የሚያካፍሉ ደራሲያን ልምድ የሚያካፍሉበት የታሪክ እና የንባብ ጉዞ በተለያዩ ከተሞች እየተካሔደ ይገኛል።
ዓመታዊው የተጓዥ ኪነ ጥበብ የታሪክ እና የንባብ መርሐ ግብር ሴቶችን እና
ህጻናትን ያካተተ ሲሆን፣ዓለም አቀፍ የሕፃናት፣የሴቶች እና የእናቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ እንደሆነም ካገኘነው መረጃ ለመረዳት ችለናል።
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት፣ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ባይራ ትሬዲንግ በጋራ ባዘጋጁት መርሐ ግብር አንጋፋዎቹ ደራሲያን ዘነበ ዎላ ደራሲና ተዋናይ ሥዩም ተፈራ፣ ገጣሚያንና ጋዜጠኞች የንባብና የባህል ግንዛቤን ለህዝቡ ለማድረስ እንደሆነ ካገኘነው መረጃ ለመረዳት ችለናል።
በአንጋፋ ደራሲያንና አርቲስቶች እንዲሁም ጋዜጠኞች የተመራ የኪነ ጥበብ ልዑካን ቡድን ታሪካዊ የንባብ ተሞክሮ ጉዞውን በሆሳዕና ከተማ የሚገኘውን የካቲት 25/67 ት/ቤት የመጎብኘት እና ታላቋ የጥበብ ሰው ገጣሚ ፊርማዬ አለሙ የተማረችበትን ት/ቤት በእርሷ ስም ማስታወሻ እንዲሆን ለመነሻ ለት/ቤቱ ቤተመጻሕፍት ከ300 በላይ መጻሕፍት ድጋፍ እንደተደረገ እና ልዑኩ በሁለተኛነት ጉዞውን ወደ ንጉሥ ካዎ ጦና ምድር በማድረግ ልምድ የማካፈልና ተፈጥሯዊ ቦታዎችን በመጎብኘት በሙያቸው ብህራቸውን በማሳል አገራቸውን ከበፊቱ በተሻለ የሚያጎሉበት በሀገሪቱ እየተሰሩ የሚገኙ ልማቶችን ተመልክተው ላላየው የማኀበረሰብ ክፍል የሚያሳዩበትን ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩበት ሲሆን በሦሥተኛና የጉብኝታቸው ፍጻሜ በውቢቷ አርባ ምንጭ እንደሚያደርጉ እና እንደጎበኟቸው ሁለቱ አገራት የአርባ ምንጭንም ጸጋ ለማኀበረሰቡ የሚያስተዋውቁበትና ለተተኪው ትውልድ ተሞክሮ የሚያጋሩበት ጉዞም እንደሚሆን እውን ነው።