ታላቅ የኪነ ጥበብ ምሽት መርሐግብር በባህርዳር ተፈሪ መኮንን ሆቴል አዳራሽ ተካሄደ

ታላቅ የኪነ ጥበብ ምሽት መርሐግብር በባህርዳር ተፈሪ መኮንን ሆቴል አዳራሽ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ታላቅ የኪነ ጥበብ ምሽት መርሐግብር በባህርዳር ተፈሪ መኮንን ሆቴል አዳራሽ አከናወነ!

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝም ቢሮ እና ከባህርዳር ዩንቨርሲቲ ጋር በመሆን "መጻሕፍት የዕውቀት ጮራ፤ መዛግብት የታሪክ አሻራ" በሚል መሪ ቃል ዓውደ ርዕይ፣ የመጻሕፍት ዓውደ ትዕይንትና ሽያጭ እና የፓናል ውይይት የንባብ ሳምንት በባህር ዳር ከተማ ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓም በይፋ መጀመሩን ተከትሎ ታላቅ የኪነ ጥበብ ምሽት መርሐግብር በባህርዳር ተፈሪ መኮንን ሆቴል አዳራሽ እሁድ ሰኔ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ተከናወነ ።

በዚህ መርሐግብር የግሽ አባይ የባህል ኪነት ባህልን መሰረት ያደረጉ ልዩ የዜማና ውዝዋዜ ስራቸውን ሲያቀርቡ በተለያዩ የሚዲያና ስነ ጽሑፍ ስራ የሚታወቁት መምህር መሠረት አበጀ፣ ዮሐንስ ገ/መድህን፣ እሌኒ ሽመልስ፣ ደምሰው መርሻ፣ የትናየት አበራ፣ ፍሬዘር ዘውዴ የቀረበ ሲሆን የባህር ዳር ዩንቨርሲቲ የፎክሎር መምህር ዶ/ር ሰለሞን ተሾመ  "ወጣትነትና ንባብ፣ ንባብና የማህበራዊ ሚዲያ ተግዳሮት" በሚል ርዕስ ጽሑፍ አቅርበዋል።

Share this Post