የኢትዮጵ ያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በአዘጋጅነት የተሳተፈበት ታላቅ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ በይፍ ተከፈተ።

የኢትዮጵ ያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በአዘጋጅነት የተሳተፈበት ታላቅ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ በይፍ ተከፈተ።

 

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር ) ከንባብ ለህይወት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ኤግዝብሽን ማዕከል ያዘጋጀው ታላቅ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ዛሬ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም በይፍ ተከፍቷል።

በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት ፣ የንባብ ለህይወት ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ከበደ፣ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ፕሬዘዳንት አቶ አበረ አዳሙ ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ተከተል ዮሐንስ ፣ አንጋፍው የታሪክ ሊቅና ተመራማሪ ኢመሪተስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ እንደዚሁም አንጋፍ ደራሲያን ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ክቡራን ታዳምያን ተገኝተውበታል።

"የምናውቀውን ነገር ደጋግመን ስንሰማው የምንሰለች ይመስለኛል፣ የምናውቀው ነገር ደጋግመን መስማትም ትዕግስታችንን ይፈታተናል ። ነገር ግን ለራሳችን ታማኝ ሆነን የምናውቀው ሚመስለንን ነገር ደጋግመን ብንመረምረው በውነት አናውቀውም።

የንበብ ጉዳይ ከርዕሱ ጀምሮ እንዲያ ይመስለኛል።

እውነት ግን ንባብ ምንድነው ቢባል ቀላል ጥያቄ አይሆንልንም ። ተግባሩ አንዳች የተፃፈ ነገር ላይ በአይን ትኩረት መመልከትን ስለሚመስል ከድርጊቱ ተነስተን ጥቂት ምላሽ ልንስጥ እንችላለን እንጂ በህይወታችን ውስጥ ባለው ዋጋ እና  በሚሰጠን የህይወት ትርጉም ልክ ልንገልጸው የሚቻለን አይደለም።

ስለዚህ የምናውቀው የሚመስለን ነገር መጠርጠር ደግ ነው።

ስለዚህ ስለ ንባብ፣ ስለ ንባብ ባህል ፣ ታላላቅ መጻሕፍትን አንብቦ ስለመረዳት ፣ ከንባብ በኋላ ሊኖር ስለሚገባው ጥልቅ እውይይት እንደገና ማሰብ፣ እንደገና መመርመር ጠለቅ ያሉ የንበብ ልምዶችን አስተውሎ ማየት እጅግ የተገባ ተግባር ነው:: " ያሉት አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት የአውደ ርዕዩን መከፈት በይፍ ባበሰሩበት ወቅት ነው፡፡

አክለውም በአዘጋጅነት የተሳተፉትን የንባብ ለህይወት ፕሮጀክት አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ፕ/ት አቶ አበረ አዳሙ ወመዘክር ካፈራቸው አንጋፍ ደራሲያንና መምህራን መካከል በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙትን ጋሽ ደራሲ ኃይለ መለኮት መዋዕልን ጠቅሰው  ተቋሙን አመስግነዋል ።

ኢመሪተስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴም ባደረጉት ንግግር "ሁለተኛ ትምህርት ቤቴ" ሲሉ በግለ ታሪካቸው ላይ የገለፁትንና የማይተካ ሚና ያለውን የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ( ወመዘክር ) በህይወታቸው ትልቅ ስፍራ እንደሚሰጡት ገልጸው አመስግነዋል ።በመጨረሻም የንባብ አውደርዕዪ እስከ ሐምሌ 27/ 2017 እንደሚቆይ በመርሀግብሩ ላይ ተመላክቷል ።

Share this Post