አዲሱ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ከማኔጅመንት አባላት ጋር ይፋዊ ትውውቅ አደረጉ፡፡

አዲሱ የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰርፀ ፍሬስብሀት ከተቋሙ የማኔጅመንት አባላት ጋር ይፋዊ ትውውቅ አደረጉ፡፡

አቶ ሰርፀ ፍሬስብሀት ከሰኔ 25/2017ዓ.ም ጀምሮ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ከአገልግሎቱ የማኔጅመንት አባላት ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡

ተቋሙ እንደነ ሲልቪያ ፓንክረስት፣ የታሪክ ጸሐፊው ተክለጻዲቅ መኩሪያና ሌሎችም የሀገራችን ታላላቅ ሰዎች በመምራት እዚህ ያደረሱት ተቋም እንደሆነም ኃላፊ አቶ ሰርፀ በትውውቁ ላይ ተናግረዋል፡፡

አዲሱ የሚመሩት ተቋም የሚሰራቸውን ሥራዎች በቅርበት እንደሚከታተሉ፤ ለእርሳቸው ሩቅ እንዳልነበረና የሚያውቁት  መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በተቋሙ የቀድሞ ኃላፊ አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉና የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመለየት ለማስተካከል ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡

Share this Post