ተቋሙ በሚስተር አርተር ማርቲሮሲያን እና ሌሎች አባላት ባሉት ልዑክ ተጎበኘ፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት በሚስተር አርተር ማርቲሮሲያን የአርሜኒያ ሪፐብሊክ የትምህርት፣ የሳይንስ፣ የባህል እና ስፖርት ምክትል ሚኒስትር፣ በሚስተር ሳሃክ ሳርግስያን በኢትዮጵያ የአርሜኒያ ሪፐብሊክ አምባሳደር፣ በዳቪት ፎጎሰያን (ዶ/ር) የአርሚኒያ የታሪክ ሙዚየም ዳይሬክተር እና ሌሎች አባላት ባሉት ልዑክ ተ ጎብኝቷል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው ከስራ ክፍል ኃላፊዎች ጋር በመሆን ለሚስተር አርተር ማርቲሮሲያን የአርሜኒያ ሪፐብሊክ የትምህርት፣ የሳይንስ፣ የባህል እና ስፖርት ምክትል ሚኒስቴርና ለልዑካኖቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በመቀጠልም አቶ አባተ ካሳው ባደረጉት ጉብኝት የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው በቀጣይ በሚኖረው የትብብር መስኮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
በኢትዮጵያ የአርሜኒያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሚስተር ሳሃክ ሳርግስያን በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና የአርሜኒያ ሪፐብሊክ በሚያደርጉት የሁለትዮሽ ግንኙነት የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ወሳኝ ቦታ ይይዛል ብለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከአርሜኒያ ኤምባሲ ጋር በስነጽሁፍ ቅርሶች ጥበቃና እንክብካቤ፣ በጥናትና ምርምር፣ በድጅጂታይዜሽን ስራና በሌሎችም መስኮች ትብብር እንደሚደረግ ከጽ/ቤት ኃላፊው ተጠቁሟል።