የንባብ ክበባት ምሥረታ የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረክ ተደረገ።

የኢትዩጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በደሴ ከተማ የትምህርት ቤቶች የንባብ ክበባት ምሥረታ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መርሐ ግብር በደሴ ከተማ አካሒዷል።

በመርሐ ግብሩ የአገልግሎቱ የጽ/ቤት ኃላፊ፣የደሴ ከተማ የትምህርት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ራሔል ታረቀ እና የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት አበበ ተገኝተዋል። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር በወ/ሮ ራሔል ታረቀ ሲደረግ የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር፣የመጽሐፍ ድጋፍ በከተማው ለሚገኝ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት ቤትና ለአንድ ትምህርት ቤት ሲደረግ መጽሐፍቶቹን አቶ አባተ ለት/ት መምሪያ ኃላፊዋ አበርክተው መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።

Share this Post