ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ
ሙስናን በሚመለከት የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ! በሚል መሪ ቃል የተከበረውን የጸረ ሙስናን ቀን ምክንያት በማድረግ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት በጋራ በመሆን በሙስናና ብልሹ አሰራር ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመከላከል የሚያስችል ሶስተኛው ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት አዳራሽ የካቲት 27/2017 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡በስልጠናው የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የጸረ አበረታች ተቋም ባለሙያዎች የተሳተፉበት ነበር።
ስልጠናውን ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ለዘርፉ ቅርበት ያላቸውና በዘርፉ እየሰሩ የሚገኙ ዶ/ር ተሾመ በላይነህ እና ዶ/ር ሳምሶን ወንድይራድ የሰጡ ሲሆን ስልጠናው ዓላማ ያደረገው የሙስና ወንጀል ምንነት፤የሙስና ወንጀል ዓይነቶች፤ የሙስና ወንጀል ባህሪያቶች፤ አዋጅ ቁጥር 881/2007 የተደነገጉ የሙስና ወንጀሎች ምንነት እንዲሁም በተቋማቶች የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችና ክፍተቶችን በማስመልከት የሚታዩ ችግሮች እና መንስኤው ላይ የባህል እና ስፖርት ዘርፉ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ያለው ተጋላጭነት በሚሉት ላይ ሰፋ ያሉ ሃሳቦችን የያዙ ሰነዶችን ለውይይት በማቅረብ ነው።
በማጠቃለያውም በቀረቡ ሰነዶች ላይ ተሳታፊዎች ሃሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎችን በማንሳት እና በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው የመዝጊያ ንግግር ተጠናቋል፡፡