ተቋሙ በመደበኛ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመረቀ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በሪከርድ ሥራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተቀናጀ  የቤተ መጻሕፍት ሙያ ስልጠና  በመደበኛ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 21 ሴት እና 8 ወንድ በድምሩ 29 ሰልጣኞችን ጥር 30/2017 ዓ.ም በተቋሙ ቅጥር ግቢ አዳራሽ አስመርቋል፡፡

ሰልጣኞቹ ከብሔራዊ ባንክ፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ከኮተቤ ሜትሮፖሊካል ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ ሚድያ ኔትወርክ፣ ከምርጫ ቦርድ እና ከግል ተቋማት የተወጣጡ እንደነበሩ ተጠቁሟል፡፡

የተቋሙ ሥራ አመራር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብነት አበራ መልዕክት ካስተላለፉ በኃላ ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት አበርክተውላቸዋል፡፡

Share this Post