አንባቢ ትውልድን ለማበረታታት ግምታቸው ከሰባት መቶ ሺህ ብር በላይ የፈጁ መጻሕፍት የተበረከተበት የንባብ ሳምንት ተካሄደ።

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከስልጤ ዞን አስተዳደር፤ ከወራቤ ዩኒቨርሲቲ፤ ከወራቤ ከተማ አስተዳደር፤ ከስልጤ ዞን ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ እና ትምህርት መምሪያ ጋር በመተባበር ከጥር 17-19 /2017 ዓ.ም “የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል የንባብ ሳምንት፣ ቡክፌር፣ ኤግዚቢሽን እና የፓናል ውይይት መድረክ በወራቤ ከተማ አካሄደ፡፡

በዚህ ዝግጅት ለአስር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቤተመጻሕፍት፣ ለአንድ የሕዝብ ቤተ-መጽሐፍ እና ለወራቤ ማረሚያ ቤት ቤተ-መጽሐፍ በቁጥር ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሰላሳ አምስት መጽሐፍት /2535/ በብር 769,032 የፈጁ መጻሕፍት ከአገልግሎቱ በስጦታ መበርከቱም ተጠቁሟል።

Share this Post