ኪን እና ስየማ፤ ኢትዮጵያዊ የትምህርት ዘይቤ በለቀማ በወር ወንበር ቅኝት

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር)፤ ሀሳብ፣ልምድ እና እውቀት የሚያጋራበት የወር ወንበር መርሐግብር ታህሳስ19 ቀን 2017 ዓ.ም በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደስላሴ አዳራሽ ተዘርግቷል።

የወሩ ወንበር ሐተታ ኪን እና ስየማ ፤ ኢትዮጵያዊ የትምህርት ዘይቤ በለቀማ የተሰኘ ሲሆን የወሩ ተናጋሪም ይህን ወርሐዊ የሀሳብ ልውውጥና ማጋሪያ መድረክ መስራች የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ናቸው።

በእለቱ አቶ ይኩኖአምላክ ኢትዮጵያዊ የትምህርት ዘይቤ፣ ኪን እና ስየማ በሚሉ አብይ ጉዳዮች መነሻ ኢትዮጵያዊ የትምህርት ዘይቤ ጥልቀት፣ መራቀቅና ማስቀጠል እንዲሁም ኪን ከላቀ ጥልቅ ሀሳብና ፍልስፍና አንጻር እንዲሁም ስየማ በእውቀትና ንድፈ ሀሳባዊነቱ የሚሉት ላይ ሰፊ ትንታኔ ሰጥተዋል።

አቶ ይኩኖአምላክ ላነሷቸው ሀሳቦች ቀደምት የፍልስፍና እና የቋንቋ በተለይም የሰዋስው ትርጓሜና አስተምህሮትንና ያሬዳዊ ዜማን በማብራሪያነት አቅርበዋል።

በወር ወንበር ልማድ መሰረት ታዳሚዎች ጥያቄዎቻቸውን ብሎም ሀሳባቸውን በማጋራት በእለቱ ተናጋሪ ተጨማሪ ትንታኔዎች ተሰጥቶበታል።

Share this Post