ተቋሙ ባስለማው ሶፍትዌር ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ለማኔጅመንት አባላትና ለጸሐፊዎች የILARMS ሶፍትዌር ስልጠና ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ተጀምሯል። የILARMS (Integrated Library, Archive and Record Management System) ሶፍትዌር የቤተ መጻሕፍት እና የመዛግብት እንዲሁም የሰነድ አስተዳደርን ማስተዳደር የሚያስችል ብሎም የተቋሙን የውስጥ ማስታወሻ ልውውጥና ከውጪ ወደ ተቋሙ የሚመጡ ዘመናዊ የዲጂታል አያያዝ እንዲኖረው የሚያደርግ ነው።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ይህን በስራ ላይ ውሎ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን ሶፍትዌር የተመለከተ ስልጠና ያስፈለገው በሙሉ አቅምና ትኩረት አገልግሎት ላይ ከመዋሉ ባለፈ ተቋሙ እንደስሙ በሪከርድና በመዛግብት አስተዳደር ቀዳሚ ሆኖ መገኘት እንዲችል መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ሶፍትዌር በተቋሙ ቀደም ብሎ በስራ ላይ የዋለ ሲሆን አጠቃቀሙን በተሻለ ብቃትና ጥራት በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን እንዲቻል ስልጠናው መዘጋጀቱን የተቋሙ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳውና ስልጠናውን አዘጋጅቶ እየሰጠ ያለው የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ስራአስፈጻሚ አቶ ግዛው ዋቅጅራ በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሐግብር ላይ አብራርተዋል።