ተቋሙ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ተጎበኘ፡፡

ተቋሙ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ተጎበኘ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብት እና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎትን ሲጎበኙ በጉብኝታቸውም በተቋሙ የሚገኙ ጥንታውያን የጽሑፍ ቅርሶችን፣ መዛግብትን እና የተለያዩ የመረጃ ሀብቶችን ተመልክተዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ እና ከሚመለከታቸው የስራ ክፍል ኃላፊዎች ጋር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ሰነዶችና መረጃዎች የሰነድና መዛግብት አስተዳደር ፖሊሲ እና መመሪያን በተከተለ መልኩ እንዴት መደራጀት እንዳለበት ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱም ክቡር ሚኒስትሩ ርዕሰ ጉዳዩ ቅድሚያ ከሚሰጧቸው ተግባራት መካከል መሆኑን ጠቅሰው በአጭር ግዜ ወደ ስራ ተገብቶ እንዲጠናቀቅ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ጭምር ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ስለ ሰነድና መረጃ አስተዳደር በውጭ ጉዳይ በኩል ስለተሰጠው ትኩረት አመስግነዋል፡፡

Share this Post