ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ የግዕዝ ጉባኤ ተጠናቀቀ

በደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ አለቃ ተክሌ ገብረ ሃና አዳራሽ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት፣ በደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ እና በአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ትብብር ከግንቦት 27 2014 ዓ.ም ጀምሮ "ግዕዝ ወ ጥበባት" በሚል መሪ ቃል ለሰባተኛ ጊዜ ሲካሄድ የነበረው ሀገር አቀፍ የግዕዝ ጉባኤ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ።

በጉባኤው መጠናቀቂያ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ጉባኤውን ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እና የጥናትና ምርምር ውጤታቸውን ላቀረቡ ምሁራን እንዲሁም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ገዳማት፣ አብያተ ክርስቲያናትና የክርስትና ኃይማኖት ትምህርት ቤቶች ለመጡ ልሂቃን ምስጋና አቅርበዋል። በመጨረሻም ስምንተኛውን ሀገር አቀፍ የግዕዝ ጉባኤ የወሎ ዩኒቨርስቲ ለማዘጋጀት ድርሻውን ወስዶ ሰባተኛው ሀገር አቀፍ የግዕዝ ጉባኤ ፍጻሜውን አግኝቷል።

Share this Post