የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ተጎበኘ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ተጎበኘ፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በተቋሙ በመገኘት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ 

በጉብኝታቸውም ሁሉንም የአገልግሎት ክፍሎች እንዲሁም የሚገኙትን የመረጃ ሀብቶች ማለትም ህትመት ከመጀመሩ በፊት የነበሩ ጥንታውያን ስነ ጽሁፍ፣ በሀገራችን በኢትዮጵያ ህትመት ከተጀመረ ጀምሮ ያሉትን የመረጃ ሀብቶች (በድምጽና በምስል ያሉትን ጨምሮ) እንዲሁም በርካታ የሀገር መዛግብትን ጎብኝተዋል፡፡

በሰጡት አስተያየትም “ትውልድ ይመጣል እንዲሁም ይሄዳል ሀገር ግን ትቀጥላለች” በማለት ተሰንደው የተቀመጡት መረጃዎች በሙሉ ከጥናትና ምርምር ፋይዳቸው በተጨማሪ ሀገርን ለማወቅ በሚኖራቸው ደርዘ ብዙ ጠቀሜታ ላይ በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡ በየክፍሉ የሚገኙትንም ባለሙያዎች ስራቸውን አውቀው የሚሰሩ በመሆናቸው አድናቆትን ችረዋል፡፡

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዩኩኖአምላክ መዝገቡ በበኩላቸው ይህ ጉብኝት በሀገር አቀፍ ደረጃ መልካም የንባብ ባህልን ለማዳበር እንዱሁም የመረጃ ሀብቶችን ለመጠበቅ በሚወጡ ፖሊሲዎች ላይ በጎ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

እንደ ፌደራል ተቋምነቱም ያለውን የመረጃ ሀብት ማሳየት ብቻ ሳይሆን የመረጃ ሀብት ኖሯቸው ሙያዊ ድጋፍ ለሚፈልጉ አካላት በሙሉ በባለሙያዎች ምክር ለመደገፍ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

Share this Post