ተቋሙ ከሚቺጋን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ወርክሾፕ ተጀምሯል

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ከሚቺጋን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ለተቋሙ የሰነድና መዛግብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ ባለሙያዎችና ከስራው ጋር ግንኙነት ላላቸው ለተቋሙ ባለሙያዎች ከሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ  በሰነድና መረጣ፣ምዘና እና አወጋገድ ላይ በተቋሙ ግቢ ወርክሾፕ አዘጋጅቷል።

በወርክሾፑ ሚስተር ዴቪድ ዋላስ ከሚቺጋን ዩንቨርስቲ፣ አቶ ቶማስ ስዩም ከባልቢስ፣ አቶ ሰለሞን ጠና የሰነድና መዛግብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ በዘርፉ ላይ ገለፃ የሚሰጡ ይሆናል።

በወርክሾፑ ማስጀመሪያ ላይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ከሚቺጋን ዩንቨርስቲ ጋር በትብብር የሚሰጠው ወርክሾፕ ተቋሙ በመዛግብት ዙሪያ ከሚሰራው ስራ በተለይም ከሰነድ ምዘና፣መረጣ እና አወጋገድ ጋር ተያይዞ መልካም አጋጣሚ እንደሆነና የተቋሙን ጥረትና የስራ እንቅስቃሴ የሚያግዝ መሆኑን ገልፀው ዩንቨርሲቲውንና ሚስተር ዴቪድ ዋሊስንና ሁሉንም አስተባባሪዎች አመስግነዋል።

Share this Post