መረጃዎችን ወደሚመለከተው የመረጃ ቋት ማደራጀት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
መረጃዎችን ወደሚመለከተው የመረጃ ቋት ማደራጀት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት የመረጃ ሃብቶች አዘገጃጀት፣የሕትመት ጥራት እና ለትውልድ የማስተላለፍ ሥራ ተግዳሮቶች በኢትዮጵያ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመመካከር የውይይት መድረክ ሰኔ 12/2016 ዓ.ም በተቋሙ ቅጥር ጊቢ አካሒዷል፡፡
በውይይት መድረኩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሲገኙ የመክፈቻ ንግግር በተቋሙ የመረጃ ሃብቶች ማሰባሰብ መሪ ስራ አስፈጻሚ በአቶ ስለሺ ሽፈራው ሲደረግ መረጃዎች እንደ ሀገር ብሎም እንደ አካባቢ እንዴትና በምን መልኩ እየተያዙ ለትውልዱ ማሻገር እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በምክክር መድረኩም ስለ ኢትዮጵያ እስላሚክ ሥነ-ጽሑፍ በፕሮፊሰር ዑስታዝ አደም ከሚል፣የፐብሊሸንግ ኢንዱስትሪ እድገትና መሰረታዊ የአሰራር ስርዓቶች በአቶ ወንድምኩን አለዩ፣ኢጥዮጵያ የታተመ መጽሐፍ ስብስብ ጥቅሞችን ማስተዋወቅ፣ተግዳሮቶቹን ማሰስ እና ተስፋዎችንና መፍትኤዎችን ማመላከት (ግላዊ ምዘና) በደራሲ ይታገሱ ጌትነት እንዲሁም በተቋሙ የመረጃ ሃብቶች ማሰባሰብ ዴስክ ኃላፊ በአቶ እስራኤል በዙ በአገሪቱ ቋንቋዎች የሚዘጋጁ የመረጃ ሃብቶችን ከማሰባሰብ አኳያ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተመለከተ የተዘጋጁ ጽሑፎች ለውይይት ቀርበው ከተሳታፊዎች ሃሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች ተሰንዝረዋል፡፡
በመጨረሻም በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በአቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ የምክክር መድረኩን ዓላማ እና ቀጣይነቱን አስመልክቶ ሃሳብ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡